ጉዞ ይዘዙ

  1. የመነሻ አድራሻ ያስገቡ። በነባሪ አድራሻው አስቀድሞ እዛው ካለ፣ የት የሚለውን መታ ያድርጉ

    ለላ አድራሻ ለመምረጥ አድራሻ ቀይርየሚለውን መታ ያድርጉ ወይም ካርታው ላይ ፒኑን ያንቀሳቅሱ።

  2. አስቀድመው የጉዞውን ተመን ለማየት መዳረሻዎን ያስገቡ።

    እስከ 3 ተጨማሪ ማቆሚያዎች ድረስ ማከል ይችላሉ ( የሚለውን መታ ያድርጉ)። የጉዞ ትዕዛዙን ከማረጋግገጥዎ በፊት መግባት አለባቸው።

  3. የአገልግሎት መደብ እና የክፍያ ዘዴ ይምረጡ።

    ጉዞ ካዘዙ በኋላ፣ ከጥሬ ገንዘብ ወደ ካርድ መቀየር ይችላሉ። በርካታ ካርዶች ከመለያዎ ጋር ከተገናኙ፣ ማናቸውንም መምረጥ ይችላሉ። ከማያ ገጹ በታች ምናሌውን ወደ ላይ ያንሸራቱ እና የክፍያ ዘዴውን ይቀይሩ።

  4. ተጨማሪ የጉዞ መረጃን ማከል ይችላሉ።

    “አማራጮች” ላይ ማንኛውንም የሚያስፈልግዎትን ነገር ያካትቱ፣ ለምሳሌ የልጅ የደኅንነት መቀመጫ ወይም የአየር ሙቀት መቆጣጠሪያ ያለው መኪና። የተወሰኑ አማራጮች ከተጨማሪ ክፍያ ጋር ይመጣሉ እናም በየአካባቢው ሊለያዩ ይችላሉ።

    እንዲሁም ለሹፌሩ አስተያየት መስጠት ይችላሉ። ለምሳሌ እርስዎን ለማግኘት ለእነሱ ቀላል ለማድረግ “መግብያው ጋር ጠብቀኝ” ማለት ይችላሉ።

  5. ጉዞ እዘዝ የሚለውን መታ ያድርጉ።

ከጉዞው በኋላ ለሹፌሩ ደረጃ ይስጡ። ለሹፌር የሚሰጥ ደረጃ ከእኛ ጋር ማሽከርከር መቀጠሉን ይወስናል።

መኪና በመፈለግ ላይ እያሉ የጉዞ ትዕዝዝ ለመሰረዝ፣ የማያ ገጹ በታች ጉዞ ሰርዝ የሚለውን መታ ያድርጉ።

መኪና አስቀድሞ ከተመደበ፣ ስለ መኪናው፣ ሹፌሩ እና ጉዞ መረጃ የያዘውን ከታች ያለውን ምናሌ ወደላይ ያንሸራቱ እና ጉዞ ሰርዝ የሚለውን መታ ያድርጉ።

እባክዎ መኪናው ከደረሰ በኋላ የጉዞ ትዕዛዝን ከሰረዙ ክፍያ እንዲከፍሉ እንደሚደረግ ልብ ይበሉ።