የYango የግላዊነት ማስታወቂያ

Yango የጉዞ አገልግሎት፣ የምግብ እና የጥቅል ወይም የተለያዩ ዕቃዎች ዴሊቨሪ፣ የኢ-ኮሜርስ እና የፊንቴክ አገልግሎቶችን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን የሚሰጡ የሞባይል እና ድር-ተኮር መተግበሪያዎችን (ከዚህ በኋላ «መተግበሪያ» ወይም «መተግበሪያዎች» ተብለው የሚጠሩ) አገልግሎቶችን ያቀርባል።

1. ይህየግላዊነትማስታወቂያምንድንነው?

እርስዎ የግል መረጃዎን በአደራ ሰጥተውናል፣ እኛም ይህንን ኃላፊነት በቁም ነገር እንወስደዋለን። የእርስዎን ግላዊነት ለመጠበቅ እና መረጃዎን እንዴት እንደምናስተናግድ ግልጽ ለማድረግ ቁርጠኞች ነን።

ይህ የግላዊነት ማስታወቂያ የምንሰበስበውን የግል መረጃ፣ እንዴት እና ለምን እንደምንጠቀምበት እና እንደምናጋራው እንዲሁም የመረጃው ባለቤት እንደመሆንዎ መጠን ያሉዎትን መብቶች ያብራራል።

2. የግልመረጃዎንእያሰናዳያለውማነው?

2.1 የግል መረጃዎ የሚሰናዳው እየተጠቀሙ ያሉትን አገልግሎት እርስዎ በሚገኙበት ሀገር ውስጥ በሚያቀርበው ኩባንያ ነው።

ይህ ኩባንያ በሚመለከታቸው የግላዊነት ሕጎች መሠረት የመረጃ ተቆጣጣሪ ሆኖ የሚሠራ ሲሆን፣ የግል መረጃዎች ለምን ዓላማ እንደሚሰናዱ እና የሚሰናዱበትን መንገድ ይወስናል።

ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ተቆጣጣሪዎች የግል መረጃን የማቀናበር ወይም የማሰናዳት ዓላማዎችን እና ዘዴዎችን በጋራ የሚወስኑ ከሆነ የጋራ ተቆጣጣሪዎች ተብለው ይጠራሉ። በዚህ ሁኔታ በሠንጠረዡ ውስጥ የተጠቀሰው የመጀመሪያው የጋራ ተቆጣጣሪ የመረጃው ባለቤት ሆኖ መብቶችዎን ለማስጠበቅ ኃላፊነት የሚወስደው አካል ሲሆን፣ ይህንንም አስመልክቶ የሚያነጋግሩት አካል ነው። በሁለተኛው ቦታ ላይ የተጠቀሰው የጋራ ተቆጣጣሪው መብቶችዎን ለመጠቀም የሚረዱዎትን ቴክኒካዊ መንገዶች የመስጠት ኃላፊነት ያለበት አካል ነው።

የምርትስም

ሀገር

ኩባንያ

አድራሻ

Yango

ፊንላንድ

Cabs tek Oy

Töpöhäntä 1 as. 1, 20750 Turku, Finland (ቶፖሃንታ 1 ኤኤስ 1፣ 20750 ቱርኩ፣ ፊንላንድ)

Ridetech International B.V.

Strawinskylaan 3101, 1077ZX Amsterdam, Netherlands (ስትራዊንስኪላን 3101፣ 1077ZX አምስተርዳም፣ ኔዘርላንድ)

ሁለቱ ኩባንያዎች የጋራ ተቆጣጣሪዎች ናቸው

ኖርዌይ

Sentral Oslo Cabs AS

Haavard Martinsens vei 9, 0978 Oslo, Norway (ሃቫርድ ማርቲንሰንስ ቬይ 9፣ 0978 ኦስሎ፣ ኖርዌይ)

Ridetech International B.V.

Strawinskylaan 3101, 1077ZX Amsterdam, Netherlands (ስትራዊንስኪላን 3101፣ 1077ZX አምስተርዳም፣ ኔዘርላንድ)

ሁለቱ ኩባንያዎች የመረጃ የጋራ ተቆጣጣሪዎች ናቸው

የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች

Yango GCC Electronic Transport Services LLC

08-461, The Offices 4, One Central Dubai World Trade Center, Dubai, UAE (08-461፣ ዘ ኦፊስስ 4፣ ዋን ሴንትራል ዱባይ ወርልድ ትሬድ ሴንተር፣ ዱባይ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች)

ሞሮኮ

Yango Mar SARL

1st Floor, corner building, Sidi Bennour Street and Soldat Taoufik Abdelkader Street, 20320 Casablanca, Morocco (1ኛ ፎቅ፣ ኮርነር ቡውልዲንግ፣ ሲዲ ቤኑር ጎዳና እና ሶልዳት ቶፊክ አብደልከዲር ጎዳና፣ 20320 ካሳብላንካ፣ ሞሮኮ)

ቤኒኒ

ቦትስዋና

ካሜሮን

ኮሎምቢያ

የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ

ጋና

ጓቲማላ

አይቮሪ ኮስት

ሞዛምቢክ

ናሚቢያ

ኔፓል

ፓኪስታን

ፔሩ

የኮንጎ ሪፐብሊክ

ቶጎ

ሴኔጋል

ቨንዙዋላ

ዛምቢያ

RideTechnology Global FZ-LLC

101, 1st Floor, Blvd. 4, Dubai Internet City, Dubai, UAE (101፣ 1ኛ ፎቅ፣ ጎዳና 4፣ ዱባይ ኢንተርኔት ሲቲ፣ ዱባይ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች)

አንጎላ

Ridetech - Transportes e Tecnologias LDA

59 Avenue 21 de Janeiro, Luanda, Angola (59 አቨኑ 21 ዴ ጄኔሮ፣ ሉዋንዳ፣ አንጎላ)

ቦሊቪያ

Ridetech BOL SRL

Tropical Street, Torres Alas II, Floor PB, Office 3, Santa Cruz de la Sierra, Bolivia (ትሮፒካል ጎዳና፣ ቶረስ አላስ II፣ ፎቅ ፒቢ፣ ቢሮ 3፣ ሳንታ ክሩዝ ዴ ላ ሲራ፣ ቦሊቪያ)

ኤል ሳልቫዶር

Mobile Venture El Salvador S.A DE C.V.

79 Avenida Norte y 3a Calle Poniente, Colonia Escalon #3698, San Salvador, El Salvador (79 አቤኒዳ ኖርቴ ዋይ 3ኤይ ካሌ ፖኒዬንቴ፣ ኮሎኒያ ኤስካሎን #3698፣ ሳን ሳልቫዶር፣ ኤል ሳልቫዶር)

ኢትዮጵያ

በየከተማው ያሉ የመረጃ ተቆጣጣሪዎች ዝርዝር እዚህ ላይ ይገኛል።

አዘርባይጃን

Ridetch Azarbaycan LLC

49/C Tbilisi Avenue, 7th floor, Chirag Plaza, Baku, Azerbaijan (49/ሲ ትቢልሲ አውራ ጎዳና፣ 7ኛ ፎቅ፣ ሻይራግ ፕላዛ፣ ባኩ፣ አዘርባይጃን)

ኳታር

Yango Transport Services W.L.L.

63 Airport Road, Umm Ghuwailina Zone, 1st Floor, Office No. 126, Regus, Jaidah Square, Doha, Qatar (63 አየር ማረፊያ መንገድ፣ ኡም ጉዋኢሊና ዞን፣ 1ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 126፣ ረጉስ፣ ጃይዳህ አደባባይ፣ ዶሃ፣ ኳታር)

ኦማን

Cloud World Trading LLC

P.O. Box 2505, Postal Code 130, North Aludhaybah Street, Bousher wilayah, Muscat Governorate, Oman (ፖ.ሳ.ቁ 2505፣ የፖስታ ኮድ 130፣ ሰሜን አሉድሃባህ ጎዳና፣ ቡሸር ዊላያህ፣ ሙስካት ጠቅላይ ግዛት፣ ኦማን)

ሌሎች ሀገሮች

RideTechnology Global FZ-LLC

101, 1st Floor, Blvd. 4, Dubai Internet City, Dubai, UAE (101፣ 1ኛ ፎቅ፣ ጎዳና 4፣ ዱባይ ኢንተርኔት ሲቲ፣ ዱባይ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች)

Yango Deli

አዘርባይጃን

Yango Delivery LLC

55 Khojaly Avenue, Khatai district, 1025 Baku, Azerbaijan (55 ኮጃሊ ጎዳና፣ ኻታይ ወረዳ፣ 1025 ባኩ፣ አዘርባይጃን)

አይቮሪ ኮስት

Foodtech SARL

Des Jasmins Street, Plot 30, Island 4, Lot 37, Cocody Danga, Abidjan, Ivory Coast (ዴስ ጃስሚንስ ጎዳና፣ ፕሎት 30፣ ደሴት 4፣ ሎት 37፣ ኮኮዲ ዳንጋ፣ አቢጃን፣ አይቮሪ ኮስት)

ዛምቢያ

Yango Deli ZAM Ltd.

7th Floor, Sunshare Tower, Stand No. LN-15584/1, Katima Mulilo Road, 15584 Lusaka, Zambia (7ኛ ፎቅ፣ ሰንሼር ታወር፣ መቆሚያ ቁጥር ኤል.ኤን-15584/1፣ ካቲማ ሙሊሎ መንገድ፣ 15584 ሉሳካ፣ ዛምቢያ)

ሴኔጋል

RideTechnology Global FZ-LLC

101, 1st Floor, Blvd. 4, Dubai Internet City, Dubai, UAE (101፣ 1ኛ ፎቅ፣ ጎዳና 4፣ ዱባይ ኢንተርኔት ሲቲ፣ ዱባይ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች)

ቦሊቪያ

Tech.EBiz BOL SRL

Gral. Inofuentes 1348, Murillo, Calacoto, La Paz, Bolivia (ግራል ኢኖፉዌንቴስ 1348፣ ሙሪሎ፣ ካላኮቶ፣ ላ ፓዝ፣ ቦሊቪያ)

Yango Delivery

አንጎላ

ቦሊቪያ

ኮሎምቢያ

ጋና

አይቮሪ ኮስት

ፓኪስታን

ፔሩ

ሴኔጋል

ሰርቢያ

ዛምቢያ

Yango Delivery FZ-LLC

101-Sub 1, 1st Floor, Blvd. 4, Dubai Internet City, Dubai, UAE (101-ሰብ 1፣ 1ኛ ፎቅ፣ ጎዳና 4፣ ዱባይ ኢንተርኔት ሲቲ፣ ዱባይ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች)

ሞሮኮ

Logistics Technologies Morocco SARL

265 Blvd. Zerktouni, 9th Floor, No. 92, Casablanca, Morocco (265 ጎዳና ዜርክቱኒ፣ 9ኛ ፎቅ፣ ቁጥር 92፣ ካዛብላንካ፣ ሞሮኮ)

የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች

Yango Delivery LLC

Office FLR06-06.06-5, Dubai World Trade Center, Trade Center 2, Dubai, UAE (ቢሮ ኤፍኤልአር06-06.06-5፣ ዱባይ የዓለም ንግድ ማዕከል፣ የንግድ ማዕከል 2፣ ዱባይ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች)

አዘርባይጃን

Yango Delivery LLC

55 Khojaly Avenue, Khatai district, 1025 Baku, Azerbaijan (55 ኮጃሊ ጎዳና፣ ኻታይ ወረዳ፣ 1025 ባኩ፣ አዘርባይጃን)

Yango Scooters

ኮሎምቢያ

RideTechnology Global FZ-LLC

101, 1st Floor, Blvd. 4, Dubai Internet City, Dubai, UAE (101፣ 1ኛ ፎቅ፣ ጎዳና 4፣ ዱባይ ኢንተርኔት ሲቲ፣ ዱባይ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች)

Yango Pay

አይቮሪ ኮስት

Yango CIV LLC

Riviera Mbadon, Island 20, N° 179 B, 06 P.O. Box 534 ABJ 06, Abidjan, Ivory Coast (ሪቪዬራ እምባዶን፣ ደሴት 20፣ ቁጥር 179 ቢ፣ 06 ፖ.ሳ.ቁ 534 ኤቢጄ 06፣ አቢጃን፣ አይቮሪ ኮስት)

ዛምቢያ

RideTechnology Global FZ-LLC

101, 1st Floor, Blvd. 4, Dubai Internet City, Dubai, UAE (101፣ 1ኛ ፎቅ፣ ጎዳና 4፣ ዱባይ ኢንተርኔት ሲቲ፣ ዱባይ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች)

Yango Sell & Buy

አይቮሪ ኮስት

Yango Delivery FZ-LLC

101-Sub 1, 1st Floor, Blvd. 4, Dubai Internet City, Dubai, UAE (101-ሰብ 1፣ 1ኛ ፎቅ፣ ጎዳና 4፣ ዱባይ ኢንተርኔት ሲቲ፣ ዱባይ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች)

2.2. መተግበሪያዎቻችን የሚጠቀሙት ብቸኛ የማረጋገጫ መሣሪያ Yango ID ነው። ይህ መሣሪያ በYango ID አገልግሎት የአጠቃቀም ውል ላይ እንደተገለጸው፣ የሞባይል ስልክ አገልግሎት አቅራቢዎ በሚገኝበት ሀገር ላይ በመመሥረት የተለያዩ ኩባንያዎች የሚያቀርቡት ይሆናል (ውሉን የሚከተለው አድራሻ ላይ ማግኘት ይቻላል፦ https://yango.com/legal/yangoid_tou)። እነዚህ ኩባንያዎች የግል መረጃዎን እንዴት እንደሚያሰናዱ ለማወቅ፣ እባክዎ የYango ID አገልግሎት የግላዊነት ማስታወቂያውን ይመልከቱ (ማስታወቂያውን የሚከተለው አድራሻ ላይ ማግኘት ይቻላል፦ https://yango.com/legal/yangoid_privacy_policy)።

3. የሚሰናዱትየግልመረጃዎችየትኞቹናቸው፣የሚሰናዱትስእንዴትእናለምንድንነው?

3.1 የምናሰናዳቸው የግል መረጃ ምድቦች፣ የእነዚህ መረጃዎች ምንጭ፣ የአሠራሩ ዓላማዎች እና የሂደቱ ሕጋዊ መሠረት ከታች ባለው ሰንጠረዥ ላይ ጠቀምጠዋል።

የመረጃምድቦች

ዓላማዎች

የሕግመሠረት

ስም ወይም የብዕር ስም

ስልክ ቁጥር

መለያዎን ለመመዝገብ

እርስዎን እንደ ተጠቃሚ ለመለየት እና ለመፍቀድ

ስለ ትዕዛዝዎ ከእርስዎ ጋር ለመነጋገር

ክፍያዎችዎን ለማሰናዳት

ውል

የመድረሻ ወይም የዴሊቨሪ አድራሻዎች

እርስዎ ባሉበት አካባቢ ውስጥ ለማዘዝ፣ ለመግዛት እና ዴሊቨር ለማድረግ የሚገኙ አገልግሎቶችን ወይም ቁሶችን ለማሳየት

ትዕዛዝዎን ለማስገባት፣ ለማሰናዳት እና አድራሻዎን በፍጥነት ለማጠናቀቅ

አድራሻዎችን በፍጥነት እንዲመርጡ ለማገዝ

ውል

የደንበኛ ምርጫዎች

እንደ ምርጫዎችዎ ትዕዛዝዎን ለማሰናዳት እና ለማሟላት

ውል

የክሬዲት ወይም የዴቢት ካርድ ዝርዝሮች

የኢ-ዋሌት ዝርዝሮች

የሞባይል ገንዘብ መለያ ዝርዝሮች

የክፍያ ዘዴ

ክፍያዎችዎን ለማሰናዳት

ውል

የእርስዎ ምስል

የመለያው ባለቤት እና ተሳፋሪው አንድ ዓይነት ሰው መሆናቸውን በማረጋገጥ፣ የአሽከርካሪዎችን ደኅንነት ለመጨመር (ጥሬ ገንዘብ ለሚከፍሉ አዲስ ተጠቃሚዎች ለሚያዙት የምሽት ትዕዛዝ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል)

ማንነትዎን ለአሽከርካሪው ለማረጋገጥ

ፈቃድ

የድምጽ ቀረጻ

በአደጋ ጊዜ የእርስዎን እና የአሽከርካሪውን ደኅንነት ለመጠበቅ

ደህንነትን በማረጋገጥ የሚገኝ ሕጋዊ ጥቅም

የአደጋውን ምርመራ ለማመቻቸት እና ለሕግ አስከባሪ አካሉ እና ለክስ የሚሆን ማስረጃ ለማቅረብ

ለሕዝብ ጥቅም

የደንበኛ ድጋፍ ለእርስዎ ለመስጠት

ውል

የደንበኛ ድጋፍ አገልግሎታችንን የጥራት ደረጃ ለመቆጣጠር

በሹፌሮች የሚሰጠውን አገልግሎት ጥራት ለመቆጣጠር

የአገልግሎቶቻችንን ጥራት በመቆጣጠር የሚገኝ ሕጋዊ ጥቅም

የኢሜይል አድራሻ

ስለ ትዕዛዝዎ የአገልግሎት መረጃ ለእርስዎ ለመላክ

የደንበኛ ድጋፍ ጥያቄዎን ለመቀበል እና ለማሰናዳት

ውል

ስለ እኛ እንዲሁም ስለ አጋሮቻችን ምርቶች እና ቅናሾች ለእርስዎ ለማሳወቅ

በማርኬቲንግ ውድድር ወይም በማናቸውም ሌሎች እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፉ እርስዎን ለመጋበዝ

ፈቃድ

የተጠቃሚ ዕውቂያዎች

ለሌላ ሰው ታክሲ ለማዘዝ

የጉዞ ዕቅድዎን ከታመነ ሰው ጋር ለማጋራት

ፈቃድ

በቅጾች የሚሰበሰበው መረጃ፦ ስም፣ ስልክ ቁጥር፣ የኢሜይል አድራሻ፣ የተጠቃሚ አስተያየት፣ መልዕክት፣ ደረጃ ምደባዎች ወይም ግምገማዎች

ግብረመልስ ለመቀበል

አገልግሎቶቻችንን ለማሻሻል

ግብረ መልስ ለመቀበል እና በአስተያየቱ ላይ በመመሠረት አገልግሎታችንን በማሻሻል የሚገኝ ሕጋዊ ጥቅም

የእርስዎን ንግድ ወይም የመደብር ግምገማዎች ለማተም

ፈቃድ

የአይፒ አድራሻ

የመሣሪያ መታወቂያ

የመሣሪያ ዓይነት እና ሞዴል

የሞባይል ሥርዓተ ክወና

የአሳሽ ወይም የሞባይል መተግበሪያ ዝርዝሮች

የመለያዎን እና የአይቲ ሥርዓቶቻችንን ተደራሽነት ደኅንነት ለማስጠበቅ

የሥርዓቶቻችንን እና የተጠቃሚዎቻችንን መረጃ ደኅንነት በማረጋገጥ የሚገኝ ሕጋዊ ጥቅም

ማጭበርበርን ለመከላከል

ማጭበርበርን በመከላከል የሚገኝ ሕጋዊ ጥቅም

የጂኦሎኬሽን መረጃ

የሹፌሮች ተገኝነትን ለመፈተሽ

ሹፌር ለእርስዎ ለመመደብ

እርስዎ ያሉበትን አካባቢ ለሹፌሩ ለመላክ

ውል

አካባቢዎን ለሦስተኛ ወገን ለማጋራት

ፈቃድ

የማስታወቂያ መለያ

ዒላማ የተደረጉ ማስታወቂያዎችን ለማበጀት

ፈቃድ

የYango ተጠቃሚ መታወቂያ

የትዕዛዞች ድግግሞሽ

ትዕዛዙን ለማጠናቀቅ የሚወስደው ጊዜ

ብዙ ጊዜ የታዘዙ አገልግሎቶች ወይም ዕቃዎች

ከመተግበሪያዎቹ ጋር በሚገናኙበት ጊዜ የታዩ ማያ ገጾች

አማካይ የትዕዛዝ ዋጋ

የእኛን መተግበሪያዎች እና የተጠቃሚ ተሞክሮን ለማሻሻል

ተዛማጅ ባህሪያትን ለማቅረብ

የመተግበሪያዎቻችንን የተጠቃሚ በይነገጽ ለመቀየር

መተግበሪያዎቻችንን፣ የተጠቃሚ ተሞክሮን እና አገልግሎቶቻችንን በማሻሻል የሚገኝ ሕጋዊ ጥቅም

የተጠቃሚ እንቅስቃሴን ለማርኬቲንግ ዓላማዎች ለመተንተን

የማርኬቲንግ እና የንግድ ስልታችንን ለማሻሻል

የገበያ ምርምር በማካሄድ የሚገኝ ሕጋዊ ጥቅም

በማርኬቲንግ ውድድር ወይም በማናቸውም ሌሎች እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፉ እርስዎን ለመጋበዝ

ፈቃድ

የትዕዛዝዎ ዝርዝሮች፦ የትዕዛዝ ቀን እና ሰዓት፣ መነሻ ነጥብ፣ መድረሻ ነጥብ፣ የጉዞ መስመር፣ ዋጋ፣ የክፍያ ዝርዝሮች እና የአድራሻ ዝርዝሮች

የትዕዛዞችዎን ታሪክ ለእርስዎ ለማቅረብ

የድጋሚ ትዕዛዝ ባህሪን ለማንቃት

ውል

ማጭበርበርን ለመከላከል

ማጭበርበርን በመከላከል የሚገኝ ሕጋዊ ጥቅም

የፍለጋ ታሪክ

በሌሎች ሻጮች ወይም አጋሮች ስለሚዘጋጁ ለእርስዎ አግባብነት ስላላቸው ቅናሾች ለእርስዎ ለማሳወቅ

ፈቃድ

የእኛን መተግበሪያዎች እና የተጠቃሚ ተሞክሮን ለማሻሻል

ተዛማጅ ባህሪያትን ለማቅረብ

የመተግበሪያዎቻችንን የተጠቃሚ በይነገጽ ለመቀየር

መተግበሪያዎቻችንን፣ የተጠቃሚ ተሞክሮን እና አገልግሎቶቻችንን በማሻሻል የሚገኝ ሕጋዊ ጥቅም

የትዕዛዝ ዝርዝሮች እና ታሪክ

የዕውቂያ ዝርዝሮች

የማኅበራዊ ሚዲያ መለያ

እርስዎ የሚያቀርቧቸው ወይም የደንበኛ ድጋፍ ሰጪ ቡድን የሚጠይቁት አስተያየቶች፣ አባሪዎች እና ሌሎች ዝርዝሮች

የደንበኛ ድጋፍ ለእርስዎ ለመስጠት

ውል

የውይይቶች ቀረጻ

በመተግበሪያዎች ውስጥ ወይም በሌላ መንገድ የሚደረጉ የእርስዎ ግንኙነቶች

እርስዎ ያቀረቡት ሌሎች መረጃዎች

ሕጋዊ መብቶቻችንን እና የሦስተኛ ወገኖችን መብቶችን ለመጠበቅ

አለመግባባቶችን እና ሕጋዊ ጥያቄዎችን ለመፍታት

የሚሰጠውን አገልግሎት ጥራት ለመቆጣጠር

መብቶቻችንን ለመጠበቅ፣ አለመግባባቶችን ለመፍታት እና የአገልግሎቶቻችንን ጥራት በመቆጣጠር የሚገኝ ሕጋዊ ጥቅም

ለ Yango Pay ተጠቃሚዎች ብቻ

ፎቶ

የብሔራዊ መታወቂያዎ ስካን

የብሔራዊ መታወቂያ ዝርዝሮች፦ ዓይነት፣ ቁጥር፣ የወጣበት ሀገር

ስም

የመኖሪያ አድራሻ

የመኖሪያ አድራሻ ማረጋገጫ

የትውልድ ቀን

ስልክ ቁጥር

የኢሜይል አድራሻ

ለተጨማሪ የደኅንነት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

መለያዎን ለመመዝገብ

ውል

በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አድርጎ የማስመሰል ወንጀል ድርጊትን የመከላከል እና የደንበኛዎን ይወቁ አሠራር ማረጋገጫዎችን ለማካሄድ

ሕጋዊ ግዴታ

ማጭበርበርን ወይም የማንነት ስርቆትን ለመከላከል

ማጭበርበርን በመከላከል የሚገኝ ሕጋዊ ጥቅም

የክሬዲት ወይም የዴቢት ካርድ ዝርዝሮች

የባንክ መለያ ዝርዝሮች

የሞባይል ገንዘብ መለያ ዝርዝሮች

ክፍያዎችን፣ ወጪ እና ገቢ ለማድረግ

ውል

በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አድርጎ የማስመሰል ወንጀል ድርጊትን ከመከላከል ጋር እና ከደንበኛዎን ይወቁ ማረጋገጫዎች ጋር የተያያዙ ሁኔታዎች እና ሌሎች መረጃዎች (ይህን መረጃ የምናገኘው ማረጋገጫውን ከሚያካሂዱ አጋሮች ነው)

መለያዎን ለመመዝገብ

የYango Pay ተግባራዊነትን እንዲጠቀሙ ለማስቻል

ውል

የYango ተጠቃሚ መታወቂያ

የአጋር ተጠቃሚ መታወቂያ

የመለያ መታወቂያ

የመለያ ሁኔታ

ቀሪ ሒሳብ

ወጪዎች

ገቢዎች

የግብይት ቀን እና ሰዓት

ነጋዴ ወይም የግብይቱ ዓላማ

የግብይት መጠን እና ሁኔታ

የግብይት መታወቂያ

የግብይት ታሪክ

የተከፈለው የሒሳብ መጠን

የብድር መጠን

የዕዳ መጠን

ክፍያዎችን ለመፈጸም

የኤሌክትሮኒክ ገንዘቦችን ለመላክ፣ ለመቀበል እና ለማውጣት

ክፍያዎችን ለማሰናዳት

የመለያ መግለጫዎችን ለመቀበል

ብድር ለማግኘት

ብድር ለመክፈል ገንዘቦችን ለመቀነስ

ውል

የYango ተጠቃሚ መታወቂያ

የአጋር ተጠቃሚ መታወቂያ

የግብይት ታሪክ

የግብይት መጠን

የግብይት መታወቂያ

የክፍያ መጠን

የYango Pay የአገልግሎት ክፍያዎችን ለማስከፈል

ውል

በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አድርጎ የማስመሰል ወንጀል ድርጊትን ከመከላከል ጋር እና ከደንበኛዎን ይወቁ ማረጋገጫዎች ጋር የተያያዙ ሁኔታዎች እና ሌሎች መረጃዎች (ይህን መረጃ የምናገኘው ማረጋገጫውን ከሚያካሂዱ አጋሮች ነው)

ለተጨማሪ የደኅንነት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

የግብይት ታሪክ

ማጭበርበርን ለመከላከል

ማጭበርበርን በመከላከል የሚገኝ ሕጋዊ ጥቅም

አጠራጣሪ ግብይትን ለመለየት

አጠራጣሪ ግብይቶችን ለፋይናንስ ተቆጣጣሪዎች ሪፖርት ለማድረግ

ሕጋዊ ግዴታ

የግብይት ታሪክ

የትዕዛዝ ታሪክ

አማካይ የትዕዛዝ ዋጋ

ለብድር ብቁ መሆንዎን ለመገምገም

ውል

Yango Sell&Buy ተጠቃሚዎች ብቻ

ፎቶዎች

ቪድዮዎች

የማኅበራዊ ሚዲያ መለያ

የማስታወቂያዎችዎ መግለጫ

ማስታወቂያዎን ለማተም

ውል

ግምገማዎች

ግምገማዎን ለማተም

ፈቃድ

3.2 መለያ እንዲመዘገብ የሚከተሉት የግል መረጃዎች ግዴታናቸው፦ ስም ወይም የብዕር ስም እና ስልክ ቁጥር። በፊንላንድ እና በኖርዌይ መለያ ለመመዝገብ የኢሜይል አድራሻም ያስፈልጋል። ይህን መረጃ ላለመስጠት ከመረጡ መለያዎን መመዝገብ አይችሉም።

የYango Pay መለያ እንዲመዘገብ የሚከተሉት የግል መረጃዎች ግዴታናቸው፦ ስም፣ ስልክ ቁጥር እና ብሔራዊ መታወቂያ። ይህን መረጃ ላለመስጠት ከመረጡ መለያዎን መመዝገብ አይችሉም። ብሄራዊ መታወቂያው በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አድርጎ የማስመሰል ወንጀል ድርጊትን የመከላከል (ኤኤምኤል) እና የደንበኛዎን ይወቁ አሠራር (ኬዋይሲ) ማረጋገጫዎችን ለማካሄድ በጥቅም ላይ ይውላል። ብሔራዊ መታወቂያ ላለማቅረብ ከመረጡ መጠቀም የሚችሉት የYango Pay ውሱን ተግባራዊነቶችን ብቻ ነው።

መለያዎን ለመጠቀም የሚከተሉት የግል መረጃዎች ግዴታናቸው፦ መድረሻ ወይም የዴሊቨሪ አድራሻዎች። ይህን መረጃ ላለመስጠት ከመረጡ ትዕዛዝ ማዘዝ አይችሉም።

3.3 የግል መረጃዎ እንዲሰናዳ ፈቃድዎን አለመስጠት የሚችሉ ሲሆን፣ መተግበሪያዎቻችንን መጠቀም መቻል አለመቻልዎን አይገድበውም። በመተግበሪያዎ እና/ወይም በሀገርዎ የሚገኙ ከሆኑ እኛን በማነጋገር ወይም አውቶማቲክ መንገዶችን በመጠቀም ፈቃድዎን በማንኛውም ጊዜ መሻር ይችላሉ።

3.4 በተሽከርካሪ ውስጥ የሚደረግ ድምጽእናቪድዮመቅረጽ የአደጋ ጊዜ ባህሪ ነው። ሹፌሩ በYango የአጠቃቀም ደንቦች መሠረት ግጭት የሚለውን አዝራር በሚያነቁባቸው ልዩ በሆኑ አስጊ ሁኔታዎች፣ ግጭቶች እና አደጋዎች ላይ ብቻ ጥቅም ላይ ይውላሉ። ለግጭት አፈታት እና ለደኅንነት ሲባል ቀረጻው ከመጀመሩ በፊት ተጠቃሚውም ሆኑ ሹፌሩ ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል።

4. የግልመረጃዎእንዴትይጠበቃል?

4.1 የግል መረጃዎን ካልተፈቀደለት፣ ድንገተኛ ወይም ሕገወጥ ጥፋት፣ የማጥፋት፣ ማስተካከል፣ አላግባብ መጠቀም፣ አሳልፎ የመስጠት ወይም የማግኘት እና ከሌሎች ሕገ-ወጥ ሂደቶች ለመጠበቅ ተገቢውን ቴክኒካዊ እና ድርጅታዊ እርምጃዎችን ተግባራዊ አድርገናል።

4.2 እነዚህ የደኅንነት እርምጃዎች ሁኔታን፣ የአተገባበር ዋጋን፣ በሂደቱ ላይ የሚከሰቱ አደጋዎችን እና የሚመለከታቸውን የግል መረጃዎች ባህሪን ከግምት ውስጥ በማስገባት ተግባራዊ እንዲሆኑ የተደረጉ ነው።

4.3 የግል መረጃዎ አብዛኛውን ጊዜ ሠራተኞቻችን ሳይደርሱበት በራስ-ሰር ይሰናዳል። ሆኖም ግን እንደዚህ ዓይነት ተደራሽነት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፣ የግል መረጃውን መድረስ የሚችሉት ይህንን መረጃ ለሥራ ለመጠቀም የሚያስፈልጋቸው ሠራተኞች ብቻ ናቸው። እነዚህ ሠራተኞች የግል መረጃን ለማሰናዳት የውስጥ ደንቦችን እና ፕሮቶኮሎችን መከተል እና የግል መረጃዎን ለመጠበቅ ቴክኒካዊ እና ድርጅታዊ የደኅንነት እርምጃዎችን መከተል ይጠበቅባቸዋል።

5. የግልመረጃዎንከማንጋርእንጋራለን?

5.1 የግል መረጃዎ በመተግበሪያው ውስጥ ባሉ አገልግሎቶች አቅርቦት ላይ በቀጥታ ለሚሳተፉ አካላት ይጋራል፦

  • ትዕዛዝዎን በመቀበል እና በማስተናገድ ላይ ለሚሳተፉ እና ለተመሳሳይ ዓላማ የሶፍትዌር መፍትሄዎችን ለሚያቀርቡ አጋሮቻችን፤
  • የኤሌክትሮኒክ ግብይቶችን ለሚያመቻቹ የክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች፣ ኢ-ዋሌት አገልግሎት አቅራቢዎች እና የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ሰጪዎች፤
  • ለመድን ኩባንያዎች፤
  • የኤሌክትሮኒክ ክፍያ ተግባራዊነትን ለሚያቀርቡልን እና በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አድርጎ የማቅረብ ወንጀልን ለሚከላከሉ እና የደንበኛዎን ይወቁ ማረጋገጫዎችን ለሚያካሂዱ አጋሮቻችን፤
  • እርስዎ ለሚኖሩበት ሀገር አግባብ ከሆነ፣ ለተጠቃሚዎቻችን ቨርቩዋል የባንክ ካርዶችን ለሚሰጡ አጋሮቻችን፤
  • ለYango Pay ተጠቃሚዎች ብድር የሚሰጡ አጋሮቻችን፤
  • የማረጋገጫ መሣሪያዎችን ለሚያቀርቡልን አጋር ድርጅቶች፤
  • ሰርቨሮችን፣ የመረጃ ማከማቻዎችን እና ሌሎች የመሠረተ ልማት ተቋማትን ለሚያቀርቡልን አጋር ድርጅቶች እና ሦስተኛ ወገኖች፤ እና
  • የደንበኛ ድጋፍ አገልግሎት በመስጠት ለሚረዱን አጋር ድርጅቶች እና ሦስተኛ ወገኖች።

በግል መረጃ ማሰናዳት ሂደቱ ላይ ሊሳተፉ የሚችሉ አካላት በሚከተለው ገጽ ላይ ተዘርዝረዋል፦ https://yango.com/legal/list_of_entities_data_processing። ተሳትፏቸው እርስዎ በሚጠቀሙት አገልግሎት እና በሚጠቀሙበት ሀገር ላይ የተመሠረተ ስለሆነ፣ የተዘረዘሩት ሕጋዊ አካላት በሙሉ የግል መረጃዎን በማሰናዳት ረገድ የግድ ተሳታፊ ላይሆኑ ይችላሉ።

5.2 የግል መረጃዎ የሚመለከተው የውሂብ ተቆጣጣሪ በሚገዛበት ሕግ መሠረት የግል መረጃዎን ለመቀበል መብት ላላቸው ወገኖች ይጋራል፦

  • ለምሳሌ እርስዎ ባሉበት ሀገር እና/ወይም የእኛ ኩባንያ አካል (አጋር) ለእርስዎ አገልግሎት በሚሰጥበት ሀገር ውስጥ ባለው ሕግ መሠረት የሕግ አስከባሪ ባለሥልጣናት የግል መረጃዎን የማግኘት ሕጋዊ መብት ካላቸው ወይም የፋይናንስ ተቆጣጣሪዎች አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ወይም የገንዘብ ዝውውሮችን የመመርመር መብት ካላቸው።

5.3 የግል መረጃዎ መተግበሪያዎቻችንን እንድናሻሽል ከሚረዱን ወገኖች ጋር ይጋራል፦

  • ለምሳሌ አገልግሎቶቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ባጋጠሙዎ ቴክኒካዊ ስህተቶች ዙሪያ የተገኘ መረጃ መተግበሪያዎቻችን ለማበልጸግ ለሚሳተፉ አጋር ድርጅቶች ይጋራል።

5.4 የግል መረጃ ስለ ምርቶች፣ አገልግሎቶች እና ቅናሾች ለእርስዎ ለማሳወቅ ከሚረዱን ወገኖች ጋር ይጋራል፦

  • ለምሳሌ የማስታወቂያ ወይም የመሣሪያ መለያዎች የማስታወቂያ ወይም የትንታኔ አገልግሎቶችን ለሚሰጡን ኩባንያዎች ሊጋሩ ይችላሉ።

6. የግልመረጃዎንከማንጋርእናጋራለን?

የእርስዎን የግል መረጃ የምናጋራቸው አካላት በተለያዩ ሀገሮች ውስጥ ሊገኙ ይችላሉ።

ከእነዚህ ሀገሮች ውስጥ አንዳንዶቹ እርስዎ አገልግሎት ከሚጠቀሙበት ሀገር ጋር ተመሳሳይ የሆነ የመረጃ ጥበቃ ወይም ከመረጃ ጋር የተያያዙ መብቶች ላይሰጡ ይችላሉ። እንደዚህ ባሉ አጋጣሚዎች ወቅት መብቶችዎ እንዲከበሩ እና ጥሰት በሚያጋጥም ጊዜ እና በኋላ የግል መረጃዎ ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ አስፈላጊ ሂደቶችን እንከተላለን።

እንደዚህ ዓይነቶቹ ሂደቶች (ተፈፃሚ ለሆኑ የግላዊነት ሕጎች ተገዢ ሆነው) የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦

i) በሚመለከታቸው ባለስልጣናት በተሰጡ መደበኛ የውል አንቀጾች መረጃ ለማስተላለፍ የመረጃ ጥበቃ አንቀጾች፤

ii) የግል መረጃዎ በሚተላለፍበት እና በሚሰናዳበት ሀገር ውስጥ ባለው የአካባቢው ሕግ ግምገማ ላይ የተመሰረቱ ተጨማሪ የውል ግዴታዎች፤

iii) ብቁ ከሆነ የመረጃ ጥበቃ ባለስልጣን የሚመጣ የዝውውር ምዝገባ ወይም ፈቃድ፤ እና/ወይም

iv) ሕገ-ወጥነትን ማለትም አገልግሎቱን ከምንሰጥበት ሀገር ሕግ ጋር የማይጣጣሙ ወይም ያልተፈቀደ የግል መረጃዎን ተደራሽነት ለመከላከል የሚወሰዱ ተጨማሪ ቴክኒካዊ እና ድርጅታዊ የደኅንነት እርምጃዎች።

የግል መረጃዎ ወደሚተላለፍባቸው ሀገሮች እና ስላሉት ጥበቃዎች መረጃ ለማግኘት እኛን ማግኘት ይችላሉ።

7. የግልመረጃዎለምንያህልጊዜይያዛል?

7.1 የማሰናዳቱ ዓላማ እስከሚሳካ ድረስ የእርስዎን የግል መረጃ እናሰናዳለን።

7.2 ትክክለኛው የማቆያ ጊዜው በሚሰናዳው የግል መረጃ እና ሂደቱ በሚከናወንበት ሀገር ላይ የተመሰረተ ነው። እባክዎ በተለይ ለሀገርዎ በተለየ ሁኔታ የተዘጋጀ የመረጃ ማቆያ እና ስረዛ መመሪያን ይመልከቱ (በሚከተለው አድራሻ ይገኛል፦ https://yango.com/legal/yango_data_retention_policy ወይም እርስዎ ካሉበት አካባቢ ጋር ተዛማጅ የሆኑ የመያዣ ጊዜዎችን የሚያመለክት ሰንጠረዥ።

7.3 እንደዚህ ያለው የማሰናዳት ሥራ በሕግ የሚያስፈልግ ከሆነ ወይም የእኛን መብቶች እና ጥቅሞች አልያም የሦስተኛ ወገኖች መብቶች እና ጥቅሞችን ለመጠበቅ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ፣ በተለይም በፍርድ ቤት ሂደቶች ወቅት፣ ከመተግበሪያዎቻችን ላይ ከሰረዙት በኋላም እንኳ የግል መረጃዎን ማሰናዳታችንን ልንቀጥል እንችላለን።

መረጃን የመሰረዝ ችሎታ ሀሳብን ከመግለጽ እና ከመረጃ ነፃነት ጋር በተያያዙ ሕጎችም ሊገደብ ይችላል።

8. የእርስዎመብቶችምንምንናቸው?

በግላዊነት ሕጎች ስር ብዙ መብቶች አሉዎት። ያሉዎት መብቶች የግል መረጃዎን በምናሰናዳበት ዓላማ እና በሚመለከተው ሕግ ላይ ይመሰረታሉ።

የማረጋገጫ መሣሪያችንን ተጠቅመው ወደ መተግበሪያው ከገቡ በኋላ ሁልጊዜም ቢሆን የእርስዎን የግል መረጃ እራስዎ መድረስ፣ ማረም ወይም መሰረዝ ይችላሉ።

በመተግበሪያዎቻችን በኩል የደንበኛ ድጋፍ ሰጪ ቡድናችንን በማነጋገር የሚከተሉትን መብቶች መጠቀም ይችላሉ።

8.1 የተደራሽነትመብት

ሁልጊዜም የግል መረጃዎ ተደራሽነት ይኖርዎታል። የግል መረጃዎን ቅጂ የመጠየቅ መብት አለዎት።

8.2 የማስተካከል መብት

የተሳሳተ፣ ትክክል ያልሆነ ወይም ጊዜ ያለፈበት ነው ብለው ያመኑባቸውን መረጃዎች እንድናሻሽል ወይም እንድናስተካክል የመጠየቅ መብት አለዎት። እንዲሁም ያልተሟላ ነው ብለው ያመኑትን ማንኛውንም መረጃ እንድናሟላ የመጠየቅ መብት አለዎት።

8.3 ፈቃድየመሻርመብት

እንደዚህ ዓይነት የማሰናዳት ሥራ በፈቃድዎ ላይ ተመሥርቶ በሚካሄድባቸው ሁኔታዎች ላይ የግል መርጃዎ እንዲሰናዳ የሰጡትን ፈቃድ የመሻር መብት አለዎት።

8.4 መረጃዎንየማጥፋትመብት

አንዳንድ ሁኔታዎች ላይ የግል መረጃዎን እንድናጠፋ የመጠየቅ መብት አለዎት፣ ለምሳሌ መረጃው ከእንግዲህ ለዓላማችን የማያስፈልግ ከሆነ፣ መረጃዎን ያለ ሕጋዊ መሠረት ወይም በሕገ-ወጥ መንገድ ያሰናዳን ከሆነ፣ ፈቃድዎን ከሻሩ (መሰናዳቱ በእርስዎ ፈቃድ ላይ የተመሠረተ ከነበር)፣ መረጃዎን የሰበሰብነው በልጅነትዎ ከነበር ወይም ተፈፃሚ በሚሆኑ ሕጎች ላይ በተመሠረቱ ሌሎች ሁኔታዎች ወቅት መረጃዎ እንዲጠፋ የመጠየቅ መብት አለዎት።

8.5 ማሰናዳትንየመገደብመብት

በአንዳንድ ሁኔታዎች የግል መረጃዎን የመሰናዳት ሂደት የመገደብ መብት ያለዎት ሲሆን፣ ለምሳሌ የማስተካከል መብትዎን ለመጠቀም ከፈለጉ መረጃዎ እስከሚስተካከል ድረስ የመረጃዎን መሰናዳት እንድንገድበው መጠየቅ ይችላሉ።

8.6 የመረጃተንቀሳቃሽነትመብት

የእርስዎ የግል መረጃ በእርስዎ ፈቃድ ወይም ከእኛ ጋር በተደረገ ውል (ለምሳሌ የመተግበሪያውን ባህሪዎች ለእርስዎ ለማቅረብ) ላይ ተመሥርቶ በራስ-ሰር የሚሰናዳ ከሆነ መረጃዎን በተዋቀረ፣ በብዛት ጥቅም ላይ በሚውል እና በማሽን መነበብ በሚችል ቅርጸት የመቀበል መብት አለዎት።

8.7 የመቃወምመብት

ማሰናዳቱ መብቶችዎን የሚጥስ ነው ብለው ካሰቡ የግል መረጃዎን መሰናዳት የመቃወም መብት አለዎት። የመቃወም መብትዎን መጠቀም የሚቻለው መረጃዎን እያሰናዳን ያለነው ሕጋዊ ወይም ሕዝባዊ ጥቅሞችን መሠረት አድርገን ከሆነ ብቻ እንደሆነ እባክዎ ልብ ይበሉ።

በቡድን መለየትን ጨምሮ በራስ-ሰር ሂደት ላይ ብቻ የተመሰረተ ውሳኔ እንዳይተገበርብዎ የማድረግ መብት አለዎት።

8.8 ቅሬታየማቅረብመብት

እኛ ሁልጊዜም ቢሆን ቅሬታዎችዎን እና አስተያየቶችዎን በጥሞና ለማጤን ዝግጁ ነን። እባክዎ የደንበኛ ድጋፍ ለሚያቀበው ቡድናችን ይላኳቸው።

መብቶችዎ ተጥሰዋል ብለው ካመኑ፣ በተለምዷዊ መኖሪያ ቦታዎ፣ የሥራ ቦታዎ ወይም ጥሰቱ በተፈጸመበት ቦታ ለሚገኝ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ቅሬታ የማቅረብ መብት አለዎት።

የሚመለከታቸው የቁጥጥር ባለስልጣኖች ዝርዝር እና የመገኛ ዝርዝሮቻቸውን https://yango.com/legal/yango_list_of_sa እዚህ ማግኘት ይቻላል።

9. እኛንእንዴትማግኘትይቻላል?

9.1 እርዳታ ማግኘት ከፈለጉ ለደንበኛ ድጋፍ የሚሰጠውን ቡድን ወደ ሞባይል መተግበሪያው ከገቡ በኋላ ማነጋገር ይችላሉ።

9.2 በፊንላንድ የመረጃ ጥበቃ ጥያቄዎች ወደ Cabs tek Oy በኢሜይል ወደ cabstekfi@gmail.com መቅረብ አለባቸው።

9.3 ኖርዌይ ውስጥ መረጃ ጥበቃን ለሚመለከቱ ጉዳዮች Sentral Oslo Cabs ASን በኢሜይል oslocabs@gmail.com ማግኘት ይኖርብዎታል።

9.4. ከፊንላንድ እና ኖርዌይ ውጭ ላሉት ሀገራት የእኛን የመረጃ ጥበቃ ኦፊሰር (DPO) በኢሜይል dpo-yt@yango.com ማግኘት ይቻላል።

9.5 እባክዎ እርስዎን በፍጥነት ለመለየት እና ጥያቄዎን በብቃት ለማሰናዳት መተግበሪያችን ላይ ለመመዝገብ የተጠቀሙበትን ስልክ ቁጥር በመልዕክትዎ ውስጥ ያስገቡ።

10. ይህሰነድየሚሻሻለውእንዴትነው?

በዚህ የግላዊነት ማስታወቂያ ጉልህ ለውጦች በሚደረጉበት ጊዜ፣ ለእርስዎ ለማሳወቅ ማናቸውንም ተደራሽ መንገዶች (በመተግበሪያው ውስጥ ባሉ የግፊ ማሳወቂያዎች፣ አጭር የጽሁፍ መልዕክት ወይም ኢሜይል) ልንጠቀም እንችላለን።

የታተመበት ቀን፦ 27.05.2025.

የሰነዱ የቀድሞ ስሪት: https://yango.com/legal/yango_privacy_notice/11032025/

የሰነዱ የቀድሞ ስሪት: https://yango.com/legal/yango_privacy_notice/28022025/

የሰነዱ የቀድሞ ስሪት: https://yango.com/legal/yango_privacy_notice/17022025/