ማቆሚያዎች ያክሉ
እርስዎ ወደሥራ ሲሄዱ ልጅዎን ወደ ትምህርት ቤት ለማድረስ ወይም የእርስዎን ሁሉንም ጓደኛዎች ወደ አየር ማረፊያ ለመውሰድ በርካታ ማቆሚያዎች ያሏቸው ጉዞዎች ተመራጭ ናቸው።
ማቆሚያ ለማከልም መድረሻ ከሚያስገቡበት በስተቀኝ + ላይ መታ ያድርጉ። እስከ 3 የሚደርሱ ማቆሚያዎች ማከል ይችላሉ። እንዲሁም በጉዞ መስመርዎ ላይ የማቆሚያዎችን ቅደም ተከተል መለወጥ የሚችሉት እዚህ ነው።
ጉዞውን ካዘዙ በኋላ 3 ወይም 4 አድራሻዎች ያሉትን የጉዞ መስመር መለወጥ አይችሉም። በሌሎች ሁሉም ሁኔታዎች ላይ በጉዞው ወቅት ተጨማሪ ማቆሚያዎችን ማከል ወይም መለወጥ ይችላሉ፣ ነገር ግን ይህ መጀመሪያ ላይ የተገመተውን የጉዞ ክፍያ እንደሚለውጥ ያስታውሱ።