Yango እና Deli የግላዊነት ማሳወቂያ

Yango እና Deli የሞባይል እና የድር መተግበሪያዎች («መተግበሪያ» የሚለው ቃል ከዚህ በኋላ ለሁለቱም ጥቅም ላይ ይውላል) በዓለም ዙሪያ ቢሮዎች ባሉት ዓለም አቀፍ የአይቲ ኩባንያ የተገነቡ ናቸው።

መተግበሪያዎቻችን ከአጋሮቻችን እና ከተባባሪዎቻችን የመጓጓዣ እና የዴሊቨሪ አገልግሎቶችን እንዲያዙ ያስችሉዎታል።

1. ይህ የግላዊነት ማሳወቂያ የሚጠቅመው ለምንድን ነው ?

ግላዊነትን ለመጠበቅ ቁርጠኞች የሆንን ሲሆን፣ ስለምናደርጋቸውም እንቅስቃሴዎች እና የግል መረጃዎን ስለምናሰናዳበት መንገድ ግልጽ መሆን እንፈልጋለን።

ስለዚህ የዚህ የግላዊነት ማሳወቂያ ዓላማ የግል ውሂብዎን እንዴት እና ለምን እንደምናሰናዳ ለእርስዎ ለማሳወቅ ነው።

2. የግል መረጃዎን እያሰናዳ ያለው ማን ነው ?

2.1 የግል መረጃዎ የሚሰናዳው በሀገርዎ ውስጥ አገልግሎቱን በሚሰጠው ኩባንያ ነው።

እነዚህ ኩባንያዎች በሚመለከታቸው ግላዊነት ሕጎች መሠረት እንደ «የውሂብ ተቆጣጣሪዎች» ሆነው ይሠራሉ እንዲሁም ዓላማዎችን እና የግል መረጃዎችን የማሰናዳት ዘዴዎችን ይወስናሉ።

የምርት ስም

ሀገር

ኩባንያ

አድራሻ

Yango

ፊንላንድ

CABS TEK OY

ቦብቴይል 1. 1, 20750, ቱርኩ, ፊንላንድ

ኖርዌይ

SENTRAL OSLO CABS AS

ሃቫርድ ማርቲንስንስ ቪዬ 9, 0978 ኦስሎ, ኖርዌይ

የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች

Yango GCC Electronic Transport Services LLC

08-461, The Offices 4, One Central Dubai World Trade Center, Dubai, UAE (08-461፣ ዘ ኦፊስስ 4፣ ዋን ሴንትራል ዱባይ ወርልድ የገበያ ማዕከል፣ ዱባይ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች)

ሞሮኮ

Yango Mar SARL

1st Floor, corner building, Sidi Bennour Street and Soldat Taoufik Abdelkader Street, 20320 Casablanca Morocco (1ኛ ፎቅ፣ ኮርነር ሕንፃ፣ ሲዲ ቤኑር መንገድ እና ሶልዳት ቶፊክ አብደልካድር መንገድ፣ 20320 ካዛብላንካ ሞሮኮ)

ካሜሩን

ኮሎምቢያ

የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

ጋና

ጓቲማላ

አይቮሪ ኮስት

ሞዛምቢክ

ናሚቢያ

ፓኪስታን

ፔሩ

ኮንጎ ሪፐብሊክ

ሴኔጋል

ዛምቢያ

RideTechnology Global FZ-LLC

101, 1st Floor, Bld. 4, Dubai Internet City, Dubai, UAE (101፣ 1ኛ ፎቅ፣ ሕንፃ 4፣ ዱባይ ኢንተርኔት ሲቲ፣ ዱባይ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች)

አንጎላ

Ridetech - Transportes e Tecnologias, LDA

59 Avenue 21 de Janeiro, Luanda, አንጎላ

ቦሊቪያ

RIDETECH BOL S.R.L.

Street Tropical, Building: Torres Alas 2, Floor: PB, Office: 3, Santa Cruz, ቦሊቪያ

ኢትዮጵያ

ጂቱጂ አይቲ ሶሉሽንስ አ/ማ

አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, አራዳ ክ/ከተማ,ወረዳ 01 የቤት ቁጥር፦ 595/596/6ተኛ ቢሮ ቁጥር፦ 610

አዘርባይጃን

Ridetech Azarbaycan LLC

49/C Tbilisi Avenue, 7th floor, Chirag Plaza, Baku, Azerbaijan (49/C ትቢልሲ ጎዳና፣ 7ኛ ፎቅ፣ ቺራግ ፕላዛ፣ ባኩ፣ አዘርባይጃን)

ኳታር

Yango Transport Services W.L.L.

63 Airport Road, Umm Ghuwailina Zone, 1st Floor, Office No. 126, Regus, Jaidah Square, Doha, Qatar (63 ኤርፖርት መንገድ፣ ኡም ጉዋእሊና ዞን፣ 1ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 126፣ ሬገስ፣ ጂዳ አደባባይ፣ ዶሃ፣ ኳታር)

ሌሎች ሀገሮች

RideTechnology Global FZ-LLC

101, 1st Floor, Bld. 4, Dubai Internet City, Dubai, UAE (101፣ 1ኛ ፎቅ፣ ሕንፃ 4፣ ዱባይ ኢንተርኔት ሲቲ፣ ዱባይ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች)

Yango Deli

አይቮሪ ኮስት

Foodtech SARL

Des Jasmins Street, Plot 30, Island 4, Lot 37, Cocody Danga, Abidjan, Ivory Coast (ዴስ ጃዝሚንስ መንገድ፣ ፕሎት 30፣ አይላንድ 4፣ ሎት 37፣ ኮኮዲ ዳንጋ፣ አቢጃን፣ አይቮሪ ኮስት)

ዛምቢያ

Yango Deli ZAM Ltd.

7th floor, Sunshare Tower, Stand no. ln_15584/1, Corner of Katima Mulilo and Lubansenshi, Olympia Park, Lusaka, Zambia (7ኛ ፎቅ፣ ሰንሼር ታወር፣ ስታንድ ቁጥር ln_15584/1፣ በካቲማ ሙሊሎ እና ሉባንሴንሺ ጥግ፣ ኦሎምፒያ መናፈሻ፣ ሉሳካ፣ ዛምቢያ)

ቦሊቪያ

Tech.EBiz Bol S.R.L.

Calacoto, Calle: Inofuentes № 1348, Murillo, La Paz, Bolivia (ካላኮቶ፣ ካሌ፦ ኢኖፉዌንቴስ ቁጥር 1348፣ ሙሪሎ፣ ላ ፓዝ፣ ቦሊቪያ)

Yango Delivery

አንጎላ

ቦሊቪያ

ጋና

አይቮሪ ኮስት

ፓኪስታን

ፔሩ

ሴኔጋል

ሰርቢያ

ዛምቢያ

ፓኪስታን

Yango Delivery FZ-LLC

101-Sub 1, First floor, Bld. 4, Dubai Internet City, Dubai, the UAE (101-ሰብ 1፣ አንደኛ ፎቅ፣ ሕንፃ 4፣ ዱባይ ኢንተርኔት ሲቲ፣ ዱባይ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች)

ሞሮኮ

Logistics Technologies Morocco SARL

265 Blvd. Zerktouni, 9th Floor, No. 92, Casablanca, Morocco (265 ጎዳና ዜርክቱኒi፣ 9ኛ ፎቅ፣ ቁጥር 92፣ ካዛብላንካ፣ ሞሮኮ)

የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች

Yango Delivery LLC

Office FLR06-06.06-5 owned by Dubai World Trade Center - Trade Center 2, Dubai, UAE (ቢሮ FLR06-06.06-5 ባለቤትነቱ የዱባይ ወርልድ የገበያ ማዕከል በሆነው የገበያ ማዕከል 2፣ ዱባይ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች)

አዘርባይጃን

Yango Delivery LLC

55 Khojaly Avenue, Khatai district, Baku, 1025, Azerbaijan (55 ኮጃሊ ጎዳና፣ ካታይ ዲስትሪክት፣ ባኩ፣ 1025፣ አዘርባይጃን)

Yango ሽያጭ እና ግዢ

አይቮሪ ኮስት

Yango Delivery FZ-LLC

101-Sub 1, First floor, Bld. 4, Dubai Internet City, Dubai, the UAE (101-ሰብ 1፣ አንደኛ ፎቅ፣ ሕንፃ 4፣ ዱባይ ኢንተርኔት ሲቲ፣ ዱባይ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች)

ቦሊቪያ

ጋና

ዛምቢያ

RideTechnology Global FZ-LLC

101, 1st Floor, Bld. 4, Dubai Internet City, Dubai, UAE (101፣ 1ኛ ፎቅ፣ ሕንፃ 4፣ ዱባይ ኢንተርኔት ሲቲ፣ ዱባይ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች)

2.2 መተግበሪያዎቻችን አንድ የማረጋገጫ መሣሪያ ይጠቀማሉ። አንዴ ከተመዘገቡ በኋላ መተግበሪያዎቻችንን በምናሰራጭበት በማንኛውም ሀገር መጠቀም ይችላሉ። እነዚያን መተግበሪያዎች ለመጠቀም ካልመረጡ በስተቀር የግል ውሂብዎ ከምንሠራቸው ሌሎች መተግበሪያዎች ጋር አይጋራም።

3. ምን ዓይነት የግል መረጃ ነው የሚሰናዳው፣ የሚሰናዳውስ እንዴት እና ለምንድን ነው ?

የምናሰናዳቸው የግል ውሂብ ምድቦች፣ የዚህ ውሂብ ምንጭ፣ ዓላማዎች እና የአሰራር ሂደቱ ሕጋዊ መሠረት እንደሚከተሉት ናቸው፦

ምንጭ

የውሂብ ምድቦች

ዓላማዎች

ሕጋዊ መሠረት

እርስዎ ለእኛ የሚያቀርቡልን

ስም ወይም የብዕር ስም፣ ስልክ ቁጥር

i) እርስዎን እንደ ተጠቃሚያችን ለመለየት እና ለመፍቀድ፣ መለያዎን ለመመዝገብ እና ስለ ትዕዛዝዎ ከእርስዎ ጋር ለመነጋገር

ii) ክፍያዎችዎን ለማሰናዳት

ውል*

የትዕዛዞች አድራሻዎች

እርስዎ ባሉበት አካባቢ ውስጥ ለማዘዝ፣ ለመግዛት እና ለማድረስ የሚገኙ አገልግሎቶችን ወይም ቁሶችን ለማሳየት፣ ለማስቀመጥ፣ ለማሰናዳት እና አድራሻዎን በፍጥነት እንዲመርጡ ለማገዝ፣ ለመለያዎ ድጋፍ ለመስጠት ትዕዛዝዎን ለማሟላት

ውል*

የደንበኛ አስተያየቶች እና ምርጫዎች

እንደ ምርጫዎችዎ ትዕዛዝዎን ለማሰናዳት እና ለማሟላት

ውል*

የባንክ መረጃ

ክፍያዎችዎን ለማሰናዳት

ውል*

የእርስዎ ምስል እና የድምፅ ቅጂ

ማንነትዎን ለማረጋገጥ፣ ማንነትዎን ለሹፌሩ ለማረጋገጥ እና በተሽከርካሪው ውስጥ የእርስዎን ድምፅ እና ምስል በአደጋ ጊዜ ለመቅዳት****

i) ፈቃደኝነት**

ii) ደህንነትን ለማረጋገጥ ሕጋዊ የሆነ ፍላጎት

iii) የሕዝብ ፍላጎት

(ሕጋዊ መሠረቱ አገልግሎት በሚሰጥበት ሀገር ውስጥ ባሉት ደንቦች እና ተደራሽ በሆነው የደኅንነት ሁነታ ይወሰናል)

የኢሜይል አድራሻ

i) ስለ ትዕዛዝዎ የአገልግሎት መረጃ ለመላክ፣ በመተግበሪያዎቻችን ላይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት

ii) ስለ እኛ እንዲሁም ስለ አጋሮቻችን ምርቶች እና ቅናሾች ለእርስዎ ለማሳወቅ፣ በገበያ ውድድር ወይም በማናቸውም ሌሎች እንቅስቃሴዎች እራስዎን ለመሳተፍ።

i) ውል*

ii) ፈቃድ***

በሚሞሉ ቅፆች ውስጥ ያለ ውሂብ፦ ስም፣ ስልክ ቁጥር፣ የኢሜይል አድራሻ፣ የተጠቃሚ መልዕክት ወይም ግብረመልስ

i) ግብረመልስ ለመስጠት

ii) የደንበኛ ድጋፍ ጥያቄዎን ለማሰናዳት

iii) የእርስዎን የንግድ ሥራ እና የመደብር ግምገማዎች ለማተም

i) ግብረ መልስ ለመቀበል እና በአስተያየቱ ላይ በመመስረት አገልግሎታችንን ለማሻሻል ያለ ሕጋዊ ፍላጎት

ii) ውል*

iii) ውል*

ከመሣሪያዎ እና ከመተግበሪያዎቻችን የምንቀበላቸው

የአይፒ አድራሻ፣ የመሣሪያ መታወቂያ፣ የመሣሪያ ዓይነት እና ሞዴል፣ የሞባይል ክወና ሥርዓት፣ አሳሽ ወይም የሞባይል መተግበሪያ ዝርዝሮች

የመለያዎ እና የአይቲ ሥርዓቶቻችን መዳረሻን ደህንነት ለማስጠበቅ

የሥርዓቶቻችንን እና የተጠቃሚዎቻችንን ውሂብ ደህንነት ለማረጋገጥ ያለ ሕጋዊ ፍላጎት

የማስታወቂያ መለያ

ዒላማ የተደረጉ ማስታወቂያዎችን ለማበጀት

ፈቃድ**

የጂኦ አካባቢ ውሂብ

የሹፌሮችን ተገኝነት ለመፈተሽ፣ ሹፌር ቀጠሮ ለማስያዝ፣ ስለ አካባቢዎ መረጃ ወደ ሹፌር ለማስተላለፍ

ውል*

ከመተግበሪያዎቻችን ጋር መስተጋብር ሲፈጥሩ የሚመነጭ

የተጠቃሚ መታወቂያ፣ የትዕዛዝ ድግግሞሽ፣ ትዕዛዙን ለማጠናቀቅ የወሰደው ጊዜ፣ በብዛት የሚታዘዙ አገልግሎቶች ወይም ዕቃዎች፣ ከመተግበሪያዎቹ ጋር መስተጋብር ሲፈጥሩ የሚታዩ የማያ ገፆች ብዛት፣ አማካይ የትዕዛዝ መጠን

i) የመተግበሪያውን እና የተጠቃሚ ተሞክሮን ለማሻሻል፣ ተዛማጅ ባህሪያትን ለማቅረብ፣ የመተግበሪያዎች በይነገጽን ለማሻሻል፣ ያልተፈቀዱ ትዕዛዞችን ለመከላከል

ii) የተጠቃሚውን እንቅስቃሴ ለገበያ ዓላማዎች ለመተንተን፣ የእኛን የግብይት እና የንግድ ስትራቴጂ ለማሻሻል

iii) በግብይት ውድድሮች ወይም በሌሎች እንቅስቃሴዎች ውስጥ እርስዎን ለተሳትፎ ዝግጁ ለማድረግ

i) መተግበሪያችንን፣ የተጠቃሚ ተሞክሮን እና አገልግሎትን ለማሻሻል ያለ ሕጋዊ ፍላጎት

ii) የግብይት ምርምር ለማካሄድ ያለ ሕጋዊ ፍላጎት

iii) ፈቃድ**

የትዕዛዝዎ ዝርዝሮች፦ የትዕዛዝ ቀን እና ሰዓት፣ የመነሻ ቦታ፣ የመድረሻ ነጥብ፣ የጉዞ መሥመር፣ ዋጋ፣ የክፈያ ዘዴ፣ የመኪና ሞዴል እና የመኪና ሰሌዳ፣ የሹፌር ስም፣ የአገልግሎት አቅራቢ ዝርዝሮች

የትዕዛዝዎን ታሪክ ለእርስዎ ለማቅረብ፣ የድግግሞሽ ትእዛዝ ባህሪን ለማንቃት እና በመተግበሪያዎቻችን ላይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት

ውል*

እርስዎ ለደንበኛ ድጋፍ ቡድን ያቀርባሉ

የትዕዛዝ ዝርዝሮች እና ታሪክ፣ የዕውቂያ ዝርዝሮች፣ አስተያየቶች፣ ዓባሪዎች፣ ሌሎች በእርስዎ ውሳኔ የገለጿቸው ወይም የድጋፍ ቡድኑ በራሱ ውሳኔ የሚጠይቀው ዝርዝር መረጃ

ለእርስዎ ድጋፍ ለማቅረብ እና በመተግበሪያችን ላይ ሊኖሩ የሚችሉ ችግሮችን መፍታት እንዲችሉ ለማገዝ

ውል*

በመተግበሪያው በኩል ከእኛ የደንበኛ ድጋፍ ቡድን፣ ሹፌሮች፣ አድራሾች፣ ዴሊቨሪ ሠራተኞች፣ ወኪሎች ወይም አጋሮች ጋር ሲገናኙ የሚፈጠር

የውይይት ቅጂዎች፣ በመተግበሪያዎች ውስጥ ወይም በሌሎች መንገዶች ያሉ የእርስዎ ግንኙነቶች እና በእርስዎ የቀረበ ወይም በእኛ መተግበሪያ የመነጨ ሌላ ውሂብ

ሕጋዊ መብቶቻችንን እና የሦስተኛ ወገኖችን መብቶች ለመጠበቅ፣ አለመግባባቶችን እና ሕጋዊ የይገባኛል ጥያቄዎችን ለመፍታት፣ ኦዲት ለማድረግ፣ የሚሰጠውን አገልግሎት ጥራት ለመቆጣጠር

መብቶቻችንን ለመጠበቅ፣ አለመግባባቶችን ለመፍታት እና የአገልግሎቶቻችንን ጥራት ለመቆጣጠር ያለ ሕጋዊ ፍላጎት

Yango ሽያጭ እና ግዢ ተጠቃሚዎች ብቻ

እርስዎ ለእኛ የሚያቀርቡልን

ፎቶዎች፣ ቪድዮዎች፣ የማስታወቂያዎችዎ መግለጫ

ማስታወቂያዎን ለማተም

ውል*

ግምገማዎች

ግምገማዎን ለማተም

ውል*

* የግል መረጃው የሚሰናዳው በምንሰጠው አገልግሎቶች የፈቃድ ስምምነት የአጠቃቀም ደንቦች ላይ በተገለጸው ውል መሠረት ነው (ውሉን https://yango.com/legal/yango_mobile_agreement/ ላይ ማግኘት ይቻላል)፤ ይህም ውል በመተግበሪያው ውስጥ መለያዎን ሲፈጥሩ እና የሚሰጡትን አገልግሎቶች ሲገለገሉ የተቀበሉት ውል ነው።

** ለማንኛውም ዓይነት የግል መረጃ ማሰናዳት የእርስዎን ፈቃድ ስንጠይቅ የሚሰበሰበውን መረጃ እና ውሂቡ የሚሰበሰብበትን ዓላማ እናሳውቅዎታለን። እንደዚህ ዓይነት ፈቃድ መስጠትን አለመቀበል ይችላሉ እና ይህም መተግበሪያዎቻችንን የመጠቀም ችሎታዎ ላይ ተጽዕኖ አይኖረውም። እኛን በማነጋገር በማንኛውም ጊዜ ፈቃድዎን ማንሳት ይችላሉ።

*** አገልግሎት የምንሰጥበት ወይም የእኛ ተዛማጅነት ያለው የመረጃ ተቆጣጣሪ የተቋቋመበት ሀገር ሕግ የተወሰኑሕጋዊ ግዴታዎችን እኛ ላይ ሊጥል ይችላል። ያንን ሕግ ለማክበር የእርስዎን የግል መረጃ ማሰናዳት አለብን። የሦስተኛ ሀገር ሕግን ለማክበር ብለን የግል ውሂብን አናሰናዳም ነገር ግን የእርስዎን ሀገር (አገልግሎታችንን የሚጠቀሙበት ሀገር) እና/ወይም አገልግሎቱን የሚያቀርበው የእኛ አካል የተመሰረተበትን ሀገር (ከእርስዎ ሀገር የተለየ ከሆነ) ሕግጋት ለማክበር ብቻ ነው።

**** በተሽከርካሪ ውስጥ የሚደረግ የድምፅ ቅጂ የአደጋ ጊዜ ባህሪ ሲሆን፣ ሹፌሩ በYango የአጠቃቀም ደንቦች መሠረት የግጭት አዝራርን በሚያነቁባቸው ልዩ በሆኑ አስጊ ሁኔታዎች፣ ግጭት እና አደጋዎች ላይ ብቻ ጥቅም ላይ ይውላሉ። ለግጭት አፈታት እና ለደህንነት ሲባል ቀረጻው ከመጀመሩ በፊት ተጠቃሚውም ሆኑ ሹፌሩ ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል።

4. የእርስዎን ውሂብ ለማን እንደምናጋራ ወይም እንደምናስተላልፍ ?

4.1 የእርስዎ የግል ውሂብ ተቀባዮች

የእርስዎ የግል ውሂብ ለሚከተሉት አካላት ብቻ ነው የሚጋራው፦

i) በመተግበሪያው ውስጥ ባሉ አገልግሎቶች አቅርቦት ላይ በቀጥታ ለሚሳተፉ፦

  • ትዕዛዝዎን በመቀበል እና በማስተናገድ ላይ የሚሳተፉ እና ለተመሳሳይ ዓላማ የሶፍትዌር መፍትሄዎችን የሚያቀርቡ አጋሮቻችን፤

  • የኤሌክትሮኒክ ግብይቶችን የሚያመቻቹ የክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች እና የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ሰጪዎች፤

  • የመድን ኩባንያዎች፤

  • የማረጋገጫ መሣሪያዎችን የሚያቀርቡ የእኛ ተባባሪዎች፤

  • ሰርቨሮችን፣ የውሂብ ማከማቻዎችን እና ሌሎች የመሠረተ ልማት ተቋማትን የሚያቀርቡልን ተባባሪዎቻችን እና ሦስተኛ ወገኖች፤ እና

  • በደንበኛ ድጋፍ የሚረዱን የእኛ ተባባሪዎቻችን እና ሦስተኛ ወገኖች።

በግል መረጃ ማሰናዳት ሂደቱ ላይ ሊሳተፉ የሚችሉ አካላት በሚከተለው ገጽ ላይ ተዘርዝረዋል፦ https://yango.com/legal/affiliates_yango_group ። ሁሉም የተዘረዘሩት አካላት በእርስዎ ውሂብ መሰናዳት ውስጥ የግድ የተሳተፉ ናቸው ማለት አይደለም፣ ምክንያቱም ተሳትፏቸው እርስዎ በሚጠቀሙት አገልግሎት እና በሚጠቀሙበት ሀገር ላይ የተመሰረተ ነው። በኩባንያዎቻችን መካከል የሀገርዎን የግላዊነት ሕጎች በመጣስ የግል ውሂብን አናጋራም።

ii) ተዛማጅነት ያለው ውሂብ ተቆጣጣሪ በሚገዛበት ሕግ መሰረት የእርስዎን የግል ውሂብ የመቀበል መብት አለው፦

  • ለምሳሌ እርስዎ ባሉበት ሀገር እና/ወይም የእኛ ኩባንያ አካል (አጋር) ለእርስዎ አገልግሎት በሚሰጥበት ሀገር ውስጥ ባለው ሕግ መሠረት የሕግ አስከባሪ ባለሥልጣናት የግል መረጃዎን የማግኘት ሕጋዊ መብት ካላቸው ወይም የፋይናንስ ተቆጣጣሪዎች አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ወይም የገንዘብ ዝውውሮችን የመመርመር መብት ካላቸው። ተፈፃሚነት ካለው የግላዊነት ሕግ በሚፃረር መልኩ የእርስዎን የግል ውሂብ ለግዛት ባለስልጣናት አናጋራም።

iii) መተግበሪያችንን እንድናሻሽል ያግዘናል፦

  • ለምሳሌ አገልግሎቶቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ስላጋጠሙ ቴክኒካዊ ስህተቶች ያለ መረጃ በመተግበሪያዎቻችን ማበልጸግ ውስጥ ለሚሳተፉ አጋሮቻችን ይጋራል።

iv) ስለ ምርቶች፣ አገልግሎቶች እና ቅናሾች እንድናሳውቅዎ ያግዘናል፦

  • ለምሳሌ የማስታወቂያ ወይም የመሣሪያ መለያዎች የማስታወቂያ ወይም የትንታኔ አገልግሎቶችን ለሚሰጡን ኩባንያዎች ሊጋሩ ይችላሉ።

4.2 የግል ውሂብዎ ዓለም አቀፍ ዝውውሮች

የእርስዎን የግል ውሂብ የምናጋራቸው ወገኖች በተለያዩ ሀገሮች ውስጥ ሊገኙ ይችላሉ።

ከእነዚህ ሀገሮች ውስጥ አንዳንዶቹ እርስዎ አገልግሎት ከሚጠቀሙበት አገር ጋር ተመሳሳይ የሆነ የውሂብ ጥበቃ ወይም ከውሂብ ጋር የተያያዙ መብቶች ላይሰጡ ይችላሉ። እንደዚህ ባሉ አጋጣሚዎች ወቅት መብቶችዎ እንዲከበሩ እና በሚተላለፉበት ጊዜ እና በኋላ የግል ውሂብዎ ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ አስፈላጊ ሂደቶችን እንከተላለን።

እንደዚህ ያሉ ሂደቶች (ተፈፃሚ ለሆኑ የግላዊነት ሕጎች ተገዢ ሆነው) የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦

i) ለመረጃ ዝውውሮች በሚመለከታቸው ባለስልጣናት በሚሰጡ በመደበኛ የውል አንቀጾች ላይ ተመስርተው በውሂብ ጥበቃ ስምምነቶች ላይ የተደረጉ ቁርጠኝነቶች፤

ii) የግል መረጃዎ በሚተላለፍበት እና በሚሰናዳበት ሀገር ውስጥ ያለ አካባቢያዊ ሕግ ግምገማ ላይ የተመሰረቱ ተጨማሪ የውል ግዴታዎች፤

iii) ብቁ ከሆነ የመረጃ ጥበቃ ባለስልጣን የሚመጣ የዝውውር ምዝገባ ወይም ፈቃድ፤ እና/ወይም

iv) ሕገ-ወጥነትን ማለትም አገልግሎቱን ከምንሰጥበት ሀገር ሕግ ጋር የማይጣጣሙ ወይም ያልተፈቀደ የግል ውሂብዎን ተደራሽነት ለመከላከል ተጨማሪ ቴክኒካዊ እና ድርጅታዊ የደህንነት እርምጃዎች።

ዓለም አቀፍ የውሂብ ማስተላለፍ መስፈርቶችን እና ገደቦችን ጨምሮ የምንሰራባቸውን ሀገሮች የግላዊነት ሕጎች ሁልጊዜ እናከብራለን።

5. የግል ውሂብን ይዞ የማቆያ ጊዜዎች ምንድን ናቸው ?

5.1 የማሰናዳቱ ዓላማ እስከሚሳካ ድረስ የእርስዎን ግላዊ ውሂብ እናሰናዳለን።

5.2 ትክክለኛው የማቆያ ጊዜ በተሰናዳው የግል መረጃ እና ሂደቱ በተኪያሄደበት ሀገር ላይ የተመሠረት ነው። ለምሳሌ ከደንበኛ ድጋፍ ቡድናችን፣ ሹፌሮች ወይም አድራሾች ጋር የተደረጉ የስልክ ንግግሮች ቅጂዎች አብዛኛውን ጊዜ ከ3 ወር ላልበለጠ ጊዜ ይቀመጣሉ።

5.3 እንደዚህ ያለ ማሰናዳት በሕግ የሚያስፈልግ ከሆነ ወይም የእኛን መብቶች እና ጥቅሞች አልያም የሦስተኛ ወገኖች መብቶች እና ጥቅሞችን ለመጠበቅ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ፣ በተለይም በፍርድ ቤት ሂደቶች ወቅት፣ ከመተግበሪያው ላይ ከሰረዙት በኋላም እንኳ የግል ውሂብዎን ማሰናዳታችንን ልንቀጥል እንችላለን።

መረጃን የመሰረዝ ችሎታ ሀሳብን ከመግለጽ እና ከመረጃ ነፃነት ጋር በተያያዙ ሕጎችም ሊገደብ ይችላል።

6. የእርስዎ መብቶች ምን ምን ናቸው ?

በግላዊነት ሕጎች ስር ብዙ መብቶች አሉዎት። ለእርስዎ የሚገኙ መብቶች የእርስዎን የግል ውሂብ በምናሰናዳበት ምክንያት እና ተፈፃሚ በሚሆን ሕግ ላይ ይመሰረታሉ።

የማረጋገጫ መሣሪያችንን ተጠቅመው ወደ መተግበሪያው ከገቡ በኋላ ሁልጊዜም ቢሆን የእርስዎን የግል ውሂብ እራስዎ መድረስ፣ ማረም ወይም መሰረዝ ይችላሉ።

በመተግበሪያዎቻችን በኩል የደንበኛ ድጋፍ ሰጪ ቡድናችንን በማነጋገር የሚከተሉትን መብቶች መጠቀም ይችላሉ፦

6.1 የተደራሽነት መብት

ሁልጊዜም የግል ውሂብዎ ተደራሽነት ይኖርዎታል። የግል መረጃዎን ቅጂ የመጠየቅ መብት አለዎት።

6.2 የማረም መብት

ትክክል ያልሆነ፣ ልክ ያልሆነ ወይም ጊዜው ያለፈበት ነው ብለው የሚያምኑትን መረጃ እንድናርም ወይም እንድናስተካክል የመጠየቅ መብት አለዎት። እንዲሁም ያልተሟላ ነው ብለው ያመኑትን ማንኛውንም መረጃ እንድንሞላ የመጠየቅ መብት አለዎት።

6.3 ፈቃድን የመሰረዝ መብት

እንደዚህ ያለ ማሰናዳት በእርስዎ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ በሚሆንበት ቦታ የግል ውሂብዎን ለማሰናዳት የሰጡትን የእርስዎን ፈቃድ የመሰረዝ መብት አለዎት።

6.4 የመሰረዝ መብት

በአንዳንድ ሁኔታዎች የግል ውሂብዎን እንድንሰርዝ የመጠየቅ መብት አለዎት፣ ለምሳሌ ከአሁን በኋላ ውሂቡ ለእኛ ዓላማ የማያስፈልግ ከሆነ፣ ውሂብዎን ያለ ሕጋዊ መሠረት ወይም በሕገ-ወጥ መንገድ ያሰናዳን ከሆነ፣ ፈቃድዎን ከሰረዙ (መሰናዳቱ በእርስዎ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ ከነበረ)፣ በልጅነትዎ ጊዜ የነበረን የእርስዎን ውሂብ ከሰበሰብን ወይም ተፈፃሚ በሚሆኑ ሕጎች ላይ በተመሰረቱ ሌሎች ሁኔታዎች ወቅት።

6.5 ማሰናዳትን የመገደብ መብት

በአንዳንድ ሁኔታዎች የግል ውሂብዎን መሰናዳት የመገደብ መብት አለዎት። ለምሳሌ የማረም መብትዎን ለመጠቀም ከፈለጉ፣ እስከሚታረም ድረስ የውሂብዎን መሰናዳት እንድንገድበው መጠየቅ ይችላሉ።

6.6 የውሂብ ተንቀሳቃሽነት መብት

የእርስዎ የግል ውሂብ በእርስዎ ፈቃድ ወይም ከእኛ ጋር በተደረገ ውል (ለምሳሌ የመተግበሪያውን ባህሪዎች ለእርስዎ ለማቅረብ) ላይ በመመስረት በራስ-ሰር የሚሰናዳ ከሆነ ውሂብዎን በተዋቀረ፣ በብዛት ጥቅም ላይ በሚውል እና በማሽን መነበብ በሚችል ቅርጸት የመቀበል መብት አለዎት።

6.7 የመቃወም መብት

ማሰናዳቱ መብቶችዎን የሚጥስ ነው ብለው ካሰቡ የግል ውሂብዎን መሰናዳት የመቃወም መብት አለዎት። እባክዎ የመቃወም መብትን መጠቀም የሚቻለው ውሂብዎን ሕጋዊ ዝንባሌዎችን ወይም ሕዝባዊ ጥቅምን መሠረት አድርገን እያሰናዳን ከሆነ ብቻ እንደሆነ ልብ ይበሉ።

በቡድን መለየትን ጨምሮ በራስ-ሰር ሂደት ላይ ብቻ የተመሰረተ ውሳኔ እንዳይተገበርብዎ የማድረግ መብት አለዎት። በቡድን መለየትን ጨምሮ በራስ-ሰር ሂደት ላይ ብቻ የተመሰረቱ ውሳኔዎችን አንወስድም።

6.8 ቅሬታ የማቅረብ መብት

እኛ ሁልጊዜም ቢሆን ቅሬታዎችዎን እና አስተያየቶችዎን በጥሞና ለማጤን ዝግጁ ነን። እባክዎ ወደ የደንበኛ ድጋፍ ቡድናችን ይላኳቸው።

መብቶችዎ ተጥሰዋል ብለው ካመኑ ለሚመለከተው የቁጥጥር ባለስልጣን ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ።

የሚመለከታቸው የቁጥጥር ባለስልጣኖች ዝርዝር እና የመገኛ ዝርዝሮቻቸው (https://yango.com/legal/yango_list_of_sa) እዚህ ይገኛል።

7. እኛን እንዴት ማግኘት ይቻላል ?

7.1 የደንበኛ ድጋፍ ቡድናችንን በመለያ ከገቡ በኋላ በተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያው በኩል ማግኘት ይችላሉ።

7.2 የእኛ የመረጃ ጥበቃ መኮንን በdpo-yt@yango.com በኩል በኢሜይል መገኘት ይችላሉ። እባክዎ በእኛ መተግበሪያ ላይ ለመመዝገብ የተጠቀሙበትን ስልክ ቁጥር ያካትቱ፣ ይህ እርስዎን በፍጥነት ለመለየት ያግዘናል።

8. ይህ ሰነድ እንዴት ነው የሚሻሻለው ?

በዚህ የግላዊነት ማሳወቂያ ላይ ጉልህ ለውጦች በሚደረጉበት ጊዜ፣ ለእርስዎ ለማሳወቅ ማናቸውንም የሚገኙ መንገዶች (በመተግበሪያው ውስጥ ባሉ የግፊ ማሳወቂያዎች፣ አጭር የጽሁፍ መልዕክት ወይም ኢሜይል) ልንጠቀም እንችላለን።

የሚከናወነው በዚህ መልኩ ይሆናል፣ ለምሳሌ አዲስ የውሂብ ምድቦችን ለማሰናዳት ወይም ውሂቡው የሚሰናዳባቸው አዳዲስ ዓላማዎች ካከልን። እንደዚህ ዓይነት ለውጦች ተግባራዊ ከመደረጋቸው በፊት ማሳወቂያ ይደርስዎታል።

የታተመበት ቀን፦ 28.02.2025.

የሰነዱ የቀድሞ ስሪት: https://yango.com/legal/yango_privacy_notice/17022025/