በኢትዮጵያ ተግባራዊ የሚሆኑ ደንቦች፣ ሁኔታዎች እና ገደቦች

የሚከተሉት ደንቦች፣ ሁኔታዎች እና ገደቦች በማንኛውም የማስታወቂያ ንብረቶች ላይ ተግባራዊ ይሆናሉ፦


Yango የመረጃ አገልግሎት ሰጪ እንጂ የትራንስፖርት ወይም የታክሲ አገልግሎቶች አቅራቢ አይደለም። የትራንስፖርት አገልግሎቶች የሚቀርቡት በሦስተኛ ወገኖች ነው። ማንኛውም የሚታዩ መግለጫዎች ለመረጃ ዓላማዎች ብቻ የሚውሉ ናቸው እንጂ አቅርቦትን ወይም ቃልኪዳንን አይዙም።

አግባብነት ያለው ባጅ በሚታይበት ቦታ፣ የሚከተለው ተግባራዊ ይሆናል፦

App Store የApple Inc. የንግድ ምልክት ሲሆን፣ በአሜሪካ እና ሌሎች አገራት ውስጥ የተመዘገበ ነው።

Google Play እና የGoogle Play አርማ የGoogle LLC የንግድ ምልክቶች ናቸው።.

የሚከተሉት ደንቦች፣ ሁኔታዎች እና ገደቦች የጉዞውን ዋጋ በሚያሳዩ በማንኛውም የማስተዋወቂያ ንብረቶች ላይ ተግባራዊ ይሆናሉ፦

የሚታዩት ዋጋዎች (i) አቅርቦት ወይም ቃል ኪዳን አይደሉም፣ (ii) ግምታዊ ናቸው እንዲሁም በትራፊክ፣ የቀኑ ጊዜ፣ ተፈላጊነት እና ሌሎች ሁኔታዎች ላይ ተመስርተው ሊለያዩ ይችላሉ (iii) በኢትዮጵያ ውስጥ የYango አገልግሎት በሚገኙባቸው ቦታዎች ውስጥ የታዘዙ ጉዞዎችን የሚመለከቱ ሲሆን (iv) ለተገደበ የጊዜ ወቅት የሚሠሩ እና ያለማሳወቂያ ወይም ማንኛውም ካሳ ወይም ምትክ ሳይሰጥ ሊለወጡ ወይም ሊሻሩ ይችላሉ።

YYango የመረጃ አገልግሎት ሰጪ እንጂ የትራንስፖርት ወይም የታክሲ አገልግሎቶች አቅራቢ አይደለም። የትራንስፖርት አገልግሎቶች የሚቀርቡት በሦስተኛ ወገኖች ነው።

የሚከተሉት ደንቦች፣ ሁኔታዎች እና ገደቦች በማስተዋወቂያ ኮዶች ላይ ተግባራዊ ይሆናሉ፦

(1) አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ ይገኛል።

(2) ጥቅም ላይ ያልዋሉ የዋጋ ቅናሾችን ለማካካስ ምንም አቻ ገንዘብ አይከፈልም።

(3) ጊዜያቸው ያለፈባቸው የዋጋ ቅናሾች መታደስ አይችሉም።

(4) አንድ የዋጋ ቅናሽ የጉዞውን ሙሉ ዋጋ ካልሸፈነ ከዋጋ ቅናሹ ተግባራዊ መደረግ በኋላ ደንበኛው በYango የሞባይል መተግበሪያ በሚሰላው መሰረት የጉዞውን ዋጋ ቀሪ ሒሳብ ለመክፈል ኃላፊነቱን ይወስዳል።

(5) እነዚህ ደንብ እና ሁኔታዎች እንዲሁም በማስተዋወቂያው ኮድ የሚቀርቡ እና (ወይም) በዚህ ድህረ-ገጽ ላይ የሚገኙ ደንብ እና ሁኔታዎች እንደ ተጨማሪ መነበብ እና መረዳት አለባቸው።

(6) እነዚህ ደንቦች ያለ ምንም ማሳወቂያ እና ያለ ማንኛውም የካሳ ክፍያ በYango አገልግሎት ኦፕሬተር ሊለወጡ ይችላሉ።

ለአዲስ ተጠቃሚዎች የሚሆኑ የዋጋ ቅናሾች

30% (ከፍተኛው 120 ብር) የዋጋ ቅናሹ ለአዲስ ተጠቃሚዎች በመጀመሪያዎቹ ሦስት የኢኮኖሚ ጉዞዎች ላይ እስከ 31.12.2024 ድረስ አዲስ አበባ ውስጥ ይሠራል።

የጥቆማ ፕሮግራም
  1. Yango በሚተገበሩ ሕጎች መሰረት ፈቃድ በተሰጠው ሕጋዊ ሰው የሚቀርብ የመረጃ አገልግሎት ነው፣ እናም እንደ የትራንስፖርት ወይም የታክሲ አገልግሎቶች አቅራቢ ሊታሰብ አይገባም።
  2. የትራንስፖርት አገልግሎቶች የሚቀርቡት በሦስተኛ ወገኖች ነው።
  3. ሁኔታዎቹ ያለ ምንም ማሳወቂያ ሊለወጡ ይችላሉ።
  4. 30% (ከፍተኛው 120 ብር) የዋጋ ቅናሹ («የጓደኛ ቅናሽ») ከ06/10/2023 ጀምሮ ይሠራል፣ ጓደኛዎ የYango አዲስ ተጠቃሚ መስፈርቶችን (ከታች ይመልከቱ) እስካሟሉ ድረስ በYango መተግበሪያ ውስጥ ጓደኛዎ ቅናሹን ካነቁበት ቀን ጀምሮ ግዜው እስከሚያበቃበት ተከታታይ ሰላሳ (30) ቀናት ድረስ በሚደረግ ጉዞ ላይ መተግበር ይችላል።
  5. 15% (ከፍተኛው 60 ብር) የዋጋ ቅናሹ («የሰጪ ቅናሽ») ከ06/10/2023 ጀምሮ ይሠራል፣ ጓደኛዎ የጓደኛ ቅናሹ የተተገበረበትን ጉዞ እንዳደረጉ ከYango መተግበሪያ ማሳወቂያ ከደረሰዎት ቀን ጀምሮ ግዜው እስከሚያበቃበት ተከታታይ ሰላሳ (30) ቀናት ድረስ በሚደረግ ጉዞ ላይ መተግበር ይችላል።
  6. የጓደኛ የዋጋ ቅናሾች ብዛት በአንድ ግለሰብ ተጠቃሚ በ999 የተገደበ ነው እና የጓደኛ የዋጋ ቅናሾች ብዛት ከታለፈ በኋላ ይህ ቁጥር እንደሚጨምር ለእርስዎ የሚገለጽ ወይም በውስጥ አዋቂነት የሚታሰብ ምንም ዋስትና ወይም ቃልኪዳን አይሰጥዎትም። የYango አገልግሎት ኦፕሬተር የጓደኛ የዋጋ ቅናሾች ሲያልቁ ለእርስዎ የማሳወቅ ኃላፊነት የለባቸውም።
  7. የጓደኛ የዋጋ ቅናሽን ለጓደኛ መላክ የሚችሉት በYango መተግበሪያ የታዘዘ ቢያንስ አንድ (1) ጉዞ ያደረጉ የYango መተግበሪያ በዘፈቀደ የተመረጡ ተጠቃሚዎች ብቻ ናቸው።
  8. ማንኛውንም ጥቅም ላይ ያልዋለ ጥቅማጥቅም ለማካካስ ምንም አይነት ተመጣጣኝ ገንዘብ አይከፈልም።
  9. ጊዜያቸው ያበቃ የዋጋ ቅናሾች መታደስ ወይም መተካት አይችሉም።
  10. የዋጋ ቅናሽ የጉዞን ሙሉ ዋጋ ካልሸፈነ አግባብነት ያለው የዋጋ ቅናሽ ተቀባዩ ለጉዞው ቀሪ ዋጋ የመክፈል ግዴታ አለበት።
  11. ነባር የYango ተጠቃሚዎች (ማለትም፣ በYango መተግበሪያ ቢያንስ አንድ (1) ጉዞ ያዘዙ ተጠቃሚዎች) የጓደኛ የዋጋ ቅናሹን መጠቀም ወይም ማንኛውም ጥቅማጥቅምን መውሰድ አይችሉም።
  12. የጓደኛ የዋጋ ቅናሹ ለYango መተግበሪያ አዲስ ተጠቃሚዎች ብቻ የሚገኝ ነው (ማለትም፣ ከዚህ በፊት በYango መተግበሪያ ማንኛውንም ጉዞ አዘው የማያውቁ)።
  13. የዋጋ ቅናሽን ማንቃት ካልቻሉ ወይም በዋጋ ቅናሾች ላይ ሌሎች ችግሮች ካጋጠሙዎት እባክዎ support@yango.com ላይ ያነጋግሩ። እነዚህ ደንብ እና ሁኔታዎች እንዲሁም ከማስተዋወቂያ ኮዱ ጋር የተያያዙት ተግባራዊ ይሆናሉ።
ለYango ተጠቃሚዎች ዓለም አቀፍ አጠቃላይ የዘመቻ ደንቦች
እነዚህ ለYango ተጠቃሚዎች (የተጠቃሚ ዘመቻዎች) ጥቅም በሚካሄዱ ሁሉም የማስተዋወቂያ ዘመቻዎች ላይ የሚተገበሩ ዓለም አቀፍ አጠቃላይ ደንቦች እና ሁኔታዎች (አጠቃላይ የዘመቻ ደንቦች) ናቸው።

በእነዚህ አጠቃላይ የዘመቻ ደንቦች ውስጥ ተጠቃሚ ወይም እርስዎ ማለት በYango መሰረተ ሥርዓት ላይ በተጠቃሚነት የተመዘገበ ግለሰብ ማለት ነው።

የተጠቃሚ ዘመቻዎች በRideTechnology Global FZ-LLC፣ በሌሎች የYango ቡድን ኩባንያዎች ወይም በነሱ በተሰማሩ ሦስተኛ ወገኖች (ዓውዱ በሚጠይቀው መሰረት እኛ ወይም የኛ) ሊደራጁ ይችላሉ።

የተጠቃሚ ዘመቻዎች አላማ በYango መተግበሪያ በኩል የሚደረጉ የተሳፋሪዎችን የጉዞ ትዕዛዞች ቁጥር መጨመር ነው። በተጠቃሚ ዘመቻዎቻችን እንደተደሰቱ ተስፋ እናደርጋለን!

  1. ይህ መረጃ ለምን አስፈላጊ እንደሆነ

እባክዎ በማንኛውም የተጠቃሚ ዘመቻዎች ውስጥ ከመሳተፍዎ በፊት እነዚህን አጠቃላይ የዘመቻ ደንቦች በጥንቃቄ ያንብቡ፤ መክንያቱም ለሚከተሉት ተገዢ ስለምያደርጉ፦

● እነዚህ አጠቃላይ የዘመቻ ደንቦች በእርስዎ ላይ መች ተግባራዊ እንደሚሆኑ፤

● ልዩ የተጠቃሚ ዘመቻ ደንቦችን እንዴት እንደምናሳውቅዎ፤

● የግል ውሂብዎን ለማሰናዳት የእርስዎ ፈቃድ፤

● ከተለየ የተጠቃሚ ዘመቻ ወይም ከሁሉም የተጠቃሚ ዘመቻዎች እንዴት መርጠው መውጣት እንደሚችሉ፤

● የተጠቃሚ ዘመቻን እንዴት ማቆም፣ ማገድ ወይም መቀየር እንደምንችል፤

● የተጠቃሚ ዘመቻ ለእርስዎ እንዳይገኝ ለማድረግ መቼ መከልከል እንደምንችል።

  1. እነዚህ አጠቃላይ የዘመቻ ደንቦች መቼ ተፈጻሚ ይሆናሉ?

እነዚህ አጠቃላይ የዘመቻ ደንቦች በተጠቃሚ ዘመቻ ላይ በተመዘገቡ ቁጥር ተፈጻሚ ይሆናሉ።

ከተለየ የተጠቃሚ ዘመቻ ወይም ከሁሉም የተጠቃሚ ዘመቻዎች መርጠው ካልወጡ በስተቀር፣ እነዚህን አጠቃላይ የዘመቻ ደንቦች በመቀበል በሁሉም የተጠቃሚ ዘመቻዎች ውስጥ ለመሳተፍ ተስማምተዋል።

እነዚህን አጠቃላይ የዘመቻ ደንቦች እና ልዩ የተጠቃሚ የዘመቻ ደንቦች ማክበር አለብዎት።

  1. ልዩ የተጠቃሚ ዘመቻዎች ደንቦች

እያንዳንዱ የተጠቃሚ ዘመቻ እንደሚከተሉት ያሉ ልዩ ደንቦችም ይኖሩታል፦

● አዘጋጅ

● ክልል

● ጊዜ

● ለተጠቃሚ ዘመቻ ብቁ ለመሆን ማሟላት ያሉብዎት ሁኔታዎች

● ሽልማት

● የአሸናፊ(ዎች) ምርጫ

● ሽልማት መስጠት

● የአንድ የተወሰነ የተጠቃሚ ዘመቻ ሌሎች ልዩ ደንቦች።

የልዩ ተጠቃሚ የዘመቻ ደንቦችን በኢሜይል፣ በYango Pro መተግበሪያ፣ በYango.com ድረ ገጽ ላይ ወይም ተገቢ ነው ብለን በምንገምተው ሌላ መንገድ እናሳውቅዎታለን።

  1. በተጠቃሚ ዘመቻ ላይ እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል

እያንዳንዱ የተጠቃሚ ዘመቻ የተለየ ነው፣ ስለዚህ ምንም አይነት ሁለንተናዊ መፍትሔ የለም። ሆኖም፣ አንዳንድ ጠቃሚ ምክሮችን እነሆ። በመጀመሪያ፣ ለመሳተፍ ብቁ መሆንዎን ለማረጋገጥ እባክዎ ልዩ ደንቦቹን በደንብ ይመርምሩ። በሁለተኛ ደረጃ፣ እባክዎ ልዩ ደንቦቹ ማንኛውንም እንቅስቃሴዎች/ተግባሮች እንዲያጠናቅቁ (ለምሳሌ X ጉዞዎችን ማጠናቀቅ) የሚጠበቅብዎት መሆናቸውን ይገምግሙ እና ሁሉንም ያጠናቅቁ። እባክዎ ሁሉንም ሁኔታዎች አሟልተው ሁሉንም እንቅስቃሴዎች/ተግባሮች ቢያጠናቅቁም እንኳን ለማሸነፍ ምንም አይነት ዋስትና እንደሌለ ልብ ይበሉ። ባያሸንፉም እንኳን እንደሚደሰቱበት ተስፋ እናደርጋለን።

  1. ግብሮች

በተጠቃሚ ዘመቻ ውስጥ ሽልማት ካገኙ፣ ተፈጻሚ የሚሆን ከሆነ በራስዎ ለሽልማቱ የሚገባውን የገቢ ግብር አስልተው መክፈል አለብዎት።

  1. የግል መረጃ

እነዚህን አጠቃላይ የዘመቻ ደንቦች በመቀበል የግል መረጃዎን በRideTechnology Global FZ-LLC፣ የተወሰነ አገርን በሚመለከት በግላዊነት ማስታወቂያ (https://yango.com/legal/yangopro_privacy_notice) ውስጥ በተገለጹ ሌሎች የYango ቡድን ኩባንያዎች እና ተፈጻሚ የሚሆን ከሆነ የተጠቃሚ ዘመቻዎችን ከማካሄድ እና ለተመሳሳይ ዓላማ በመካከላቸው ያለውን መረጃ ከማስተላለፍ (የድንበር አለፍ ሽግግርን ጨምሮ) አንፃር በአዘጋጆች እንዲሰናዳ ተስማምተዋል። እኛ እና/ወይም አዘጋጅ ውጤቱን ለማስኬድ፣ ለማጠቃለል እና ሽልማቶችን ለመስጠት፣ ግብረ መልስ ለማግኘት፣ እንደ ስልክ ቁጥር፣ ሙሉ ስም፣ የጉዞ ዝርዝሮችን ጨምሮ እና/ወይም በልዩ ውሎች ውስጥ የተገለጹ ሌሎች መረጃዎች ለተጠቃሚ ዘመቻዎች አላማ ብቻ አስፈላጊ የሆኑትን ግላዊ መረጃዎችን ነው የምናሰናዳው።

እኛ እና/ወይም አዘጋጅ ሽልማቶችን ለመስጠት እና ማንኛውንም ተጨማሪ ተግባራት ከአሸናፊዎች ጋር ለመስራት እንደ ሙሉ ስም፣ የመኖሪያ አድራሻ፣ የመታወቂያ ዝርዝሮች፣ ፎቶ፣ ቪድዮ፣ የማህበራዊ አውታረ መረቦች የተጠቃሚ ስሞች ያሉ ተጨማሪ መረጃዎችን እና/ወይም በልዩ ደንቦች ውስጥ የተገለጹ ሌሎች መረጃዎች ልንጠይቅ እንችላለን።

የተጠቃሚ ዘመቻዎችን ውጤት ልናሳውቅ እንችላለን፣ ለምሳሌ የአሸናፊዎችን አንዳንድ ግላዊ መረጃዎች በድር ጣቢያችን፣ በይፋዊ መለያዎቻችን እና/ወይም በማህበራዊ አውታረመረቦች ላይ ባሉ ግሩፕዎች እና/ወይም በመተግበሪያችን ላይ ልናሳውቅ እንችላለን። እንደዚህ ባሉ ሁኔታዎች ውስጥ በሚደረጉ ልጥፎች ተስማምተዋል እና ውሂቡ ስም፣ የአባት ስም፣ ፎቶ እና/ወይም በልዩ ደንቦች ውስጥ የተገለፀ ሌላ ማንኛውም መረጃ ሊሆን ይችላል። እንዲሁም በይነ መረብ (ድር ጣቢያዎች፣ ጽሁፎች፣ ባነሮች፣ ቪድዮዎች፣ ቃለመጠይቆች) ላይ በማተም የሹፌሮች ዘመቻዎችን ትኩረት ለመሳብ ከአሸናፊዎች ጋር አንዳንድ የማርኬቲንግ እንቅስቃሴዎችን ልናደርግ እንችላለን። እንደዚህ ባሉ ሁኔታዎች ውስጥ የዚህ ወቅት አሸናፊዎችን በማነጋገር በማርኬቲንግ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳትፎን ለማዘጋጀት የሚረዳ ውሂብን ለመጠቀም ፈቃደኝነትን እንጠይቃለን። ማንኛውንም ጥርጣሬ ለማስወገድ የተሳታፊዎች ምዝገባ እና የሚመለከታቸው የግል መረጃዎች አቅርቦት ሙሉ በሙሉ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው። በማንኛውም ጊዜ ለተወሰነ የተጠቃሚ ዘመቻ ወይም ለሁሉም የተጠቃሚ ዘመቻዎች የግል ውሂብዎ እንዳይሰናዳ መርጠው መውጣት ይችላሉ። እባክዎን የውሂብ ጥበቃ ኦፊሰራችንን በኢሜይል dpo-yt@yango.com ላይ ያግኙ ወይም የድጋፍ ቡድናችን ያነጋግሩ። ለተጠቃሚ ዘመቻዎች አስፈላጊው የሂደት ጊዜ ካለቀ በኋላ፣ ለማቆየት ምንም ሕጋዊ ምክንያቶች ከሌሉ የተሰበሰቡት ግላዊ ውሂቦዎች ይሰረዛሉ/ይጠፋሉ። እኛ እና አዘጋጁ የግላዊ መረጃዎችን ምስጢራዊነት ለመጠበቅ እና እነዚህን መረጃዎች ከመጥፋት፣ ከድንገተኛ ወይም ሕገ-ወጥ ውድመት፣ ባልተፈቀደ መንገድ ይፋ ማድረግ ወይም ተደራሽነት እንዲሁም ከማንኛውም ዓይነት ሕገወጥ ማሰናዳት ለመከላከል አስፈላጊ እና ተገቢ የሆኑ ቴክኒካዊ እና ድርጅታዊ እርምጃዎችን እንወስዳለን። የተወሰኑ ወይም ሁሉም የተጠቃሚ ዘመቻዎች አሁን ያለውን አካባቢያዊ የመረጃ ጥበቃ ሕግ የሚቃረኑ ከሆኑ፣ እነዚህ አጠቃላይ ደንቦች እነዚያ የተጠቃሚ ዘመቻዎች አደረጃጀት እና አፈፃፀም ላይ ተፈጻሚ አይሆኑም እና እነዚያ የተጠቃሚ ዘመቻዎች ማንኛውንም የግል መረጃ ማስተላለፍን ጨምሮ በእነዚህ አጠቃላይ ደንቦች ወይም የየራሳቸው ልዩ ደንቦች (የሚመለከተው ከሆነ) ላይ በቀረበው መሰረት አልተደራጁም ወይም አልተከናወኑም።

  1. የአዕምሯዊ ንብረት

በተወሰኑ የተጠቃሚ ዘመቻዎች ውስጥ ለመሳተፍ እንደ ፎቶዎች፣ ምስሎች፣ ጽሁፎች እና ሌሎች የፈጠራ ሥራዎች ያሉ ኦሪጅናል አዕምሯዊ ንብረቶችን (ከዚህ በኋላ “IP” እየተባለ የሚጠራውን) መፍጠር ይኖርብዎታል። ወደ ተጠቃሚ ዘመቻው በመግባት፣ (በማንኛውም ሁኔታ RideTechnology Global FZ-LLCን ጨምሮ) አግላይ ያልሆነ፣ ዓለም አቀፍ፣ ከመጠቀም ክፍያ ነፃ የመጠቀም፣ የማባዛት፣ የማሻሻያ፣ ወደ ሌላ የመቀየር፣ የማተም፣ የመተርጎም፣ ከእሱ ላይ የሚነሱ ሥራዎችን የመፍጠር፣ የማሰራጨት፣ ትርዒት የማቅረብ፣ የማሳየት፣ ለሕዝብ የማሳወቅ (በይነመረብን ጨምሮ) እና በሌላ መልኩ የተጠቃሚ ዘመቻን ለማከናወን፣ ለሕዝብ ማሳያ፣ በሚዲያ ለማሰራጨት፣ ለማስተዋወቅ፣ እና የተጠቃሚ ዘመቻን ለማስተዳደር IPን እንድንጠቀም ፈቃድ ይሰጡናል። ይህ ፈቃድ አሁን በሚታወቅ ወይም ከዚህ በኋላ በሚመጣ ላይ የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች እስከሚቆይበት ጊዜ ድረስ IPን በማንኛውም ሚዲያ የመጠቀም መብትን ያካትታል። ይህ ፈቃድ IPን ለማናቸውም ሦስተኛ ወገኖች እነዚህን ጨምሮ ግን በእነዚህ ሳይገደብ ለተጠቃሚው ዘመቻ አጋሮች እና ስፖንሰሮች ንዑስ ፈቃድ የመስጠት መብትን ያካትታል።

አሸናፊ ሆነው ከተመረጡ፣ ሁሉንም ተዛማጅ የቅጂ መብቶችን እና ሌሎች መብቶችን ጨምሮ IP በራስ ሰር ወደ እኛ እንደሚተላለፍ ይስማማሉ። የመብቶች ማስተላለፍ ክፍያ በሽልማቱ መጠን ውስጥ ተካትቷል፣ ይህም ከሽልማቱ አጠቃላይ መጠን 10% አካትቷል።

IP ጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ ሁሉ ለሹፌሮች ተገቢውን ባለቤትነት ለማቅረብ ተስማምተን ሳለ፣ እኛ እንደዚህ ዓይነቱን ባለቤትነት የማቅረብ ግዴታ የሌለብን መሆኑን ይረዳሉ እና ዕውቅና ይሰጣሉ። ያለ ተጨማሪ ማካካሻ ወይም ማሳወቂያ የእርስዎን ምስል፣ ስም፣ ተመሳሳዩን እና ሌሎች መረጃዎችን ከተጠቃሚ ዘመቻዎች ጋር ለተገናኙ ማስተዋወቂያ እና ይፋዊ ዓላማዎች እንድንጠቀምበት መብት ሰጥተውናል።

የእርስዎ IP የአዕምሯዊ ንብረት መብቶችን ወይም ማናቸውንም የሦስተኛ ወገን መብቶችን እንደማይጥስ ወክለው ዋስትና ይሰጣሉ። በተጨማሪ እኛን (RideTechnology Global FZ-LLCን የሚያካትት ማንኛውም ጉዳይ)፣ አጋሮቻችንን እና ፈቃድ ያላቸው ሦስተኛ ወገኖችን ከዚህ ዋስትና ማንኛውም ጥሰት ከሚመጡ ወይም እዚህ በተፈቀደው መሠረት ካለ የIP አጠቃቀም ፈቃድ ከሚመነጩ ማናቸውም ይገባኛሎች፣ ጉዳቶች፣ እክሎች ወይም ወጪዎች ለመካስ እና ተጠያቂ ላለማድረግ ይስማማሉ።

  1. ከተወሰነ የተጠቃሚ ዘመቻ ወይም ሁሉም የተጠቃሚ ዘመቻዎች እንዴት መርጦ መውጣት እንደሚቻል

ለእኛ በማሳወቅ በማንኛውም ጊዜ ከተወሰነ የተጠቃሚ ዘመቻ ወይም ሁሉም የተጠቃሚ ዘመቻዎች መርጠው መውጣት ይችላሉ። በYango Pro መተግበሪያ በኩል ወይም rgbesorgbor@yandex-team.ru ላይ ለእኛ ኢሜይል በማድረግ ይህን ሊያደርጉት ይችላሉ።

  1. ማንኛውንም የተጠቃሚ ዘመቻ እንዴት ማገድ፣ ማቋረጥ ወይም መለወጥ እንደምንችል

ማንኛውንም የተጠቃሚ ዘመቻ በማንኛውም ጊዜ ላይ ልናግድ፣ ላናስቀጥል ወይም ልንለውጥ እንችላለን።

  1. ለእርስዎ የተጠቃሚ ዘመቻን ተገኚ ማድረግ ፈቃደኛ የማንሆነው መቼ ነው

ማጭበርበር እና ሌሎች መደበኛ ያልሆኑ ነገሮች ፍትሐዊ በሆነ መልኩ ነገሮችን እናድርግ! እባክዎ አያጭበርብሩ። እባክዎ ማናቸውንም የማጭበርበር እንቅስቃሴዎችን ወይም መደበኛ ያልሆኑ ነገሮችን (ከታች እንደተገለጸው) ካስተዋልን በአስቸኳይ እና ያለምንም ማሳወቂያ የሚከተሉትን ልናደርግ እንደምንችል ያስተውሉ፦

● ከተጠቃሚ ዘመቻ እርስዎን ማስወገድ

● ሙሉውን የተጠቃሚ ዘመቻ ማገድ

● ማንኛውንም ሽልማት እርስዎን ለመሸለም ፈቃደኛ አለመሆን።

የማጭበርበር እንቅስቃሴ ማለት የYango መድረክን፣ ሌሎች የYango መድረክ ተጠቃሚዎችን ወይም ማናቸውም ሦስተኛ ወገኖችን ለማጭበርበር የሚኖሩ ማናቸውም ሙከራዎች ማለት ነው (ለምሳሌ፦ የክፍያ አገልግሎት አቅራቢዎች፣ የክፍያ ካርድ አቅራቢ፣ ወዘተ)። ይህ ሐሰተኛ ወይም በቅድሚያ የተደራጁ ጉዞዎችን፤ የክፍያ መሣሪያ ያልተፈቀደ አጠቃቀም፤ በቅድሚያ የተደራጁ ጉዞዎችን፤ ዋጋ ላይ ጠጽእኖ ማድረግን ወዘተ ማመንጨትን ሊያካትት ይችላል።

መደበኛ ያልሆኑ ነገሮች ማለት ከYango መድረክ ጋር የሚደረጉ ማናቸውም ያልተለመዱ መርሐብሮች ናቸው። ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ ይህ የራስ ትዕዛዞችን፣ ከተመሳሳይ ተሳፋሪ ጋር ብዙ ተከታታይ ጉዞዎችን (መሳርያ ወይም የክፍያ መሣሪያዎች)፣ የማስተዋወቂያ ኮዶችን ከመጠን በላይ መጠቀም፣ ያልተለመዱ ጉዞዎች (ለምሳሌ፦ ከተመሳሳይ አካባቢ የሚጀምሩ ከመጠን በላይ የሆኑ ጉዞዎች ወይም ባልተለመደ ሁኔታ በርቀት ወይም በጊዜ ረዥም ወይም አጭር የሆኑ ከመጠን በላይ የሚሆኑ ጉዞዎች)፤ የክፍያ ችግሮች ያሉባቸው ጉዞዎች (ክፍያ ተመላሽ ማድረጎች፣ የክፍያ መንገድ አለመሳካቶች፣ ወዘተ)።

  1. እነዚህን የአጠቃላይ ዘመቻ ደንቦች ወይም የልዩ ተጠቃሚ ዘመቻ ደንቦች የመለወጥ መብታችን

እነዚህን የአጠቃላይ ዘመቻ ደንቦች ወይም የልዩ ተጠቃሚ ዘመቻ ደንቦች በማንኛውም ጊዜ ላይ እና ያለምንም ቅድሚያ ማሳወቂያ ልናሻሽለው እንችላለን። ማናቸውንም እንደዚህ ዓይነት ለውጦች እርስዎ በሚመዘገቡባቸው ማናቸውም የተጠቃሚ ዘመቻዎች ላይ በአስቸኳይ ይተገበራሉ።

  1. ሕጋዊ አካሎች እና ክፍሎች

በእነዚህ የአጠቃላይ ዘመቻ ደንቦች እና ልዩ የተጠቃሚ ዘመቻ ደንቦች መካከል ወጥነት በማይኖርበት ሁኔታ ላይ የልዩ ተጠቃሚ ዘመቻው ተግባራዊ ይሆናሉ።

የተጠቃሚ ዘመቻ ልዩ ደንቦች ለYango ተጠቃሚዎች «[የዘመቻው ስም]»

ይህ የተጠቃሚ ዘመቻ ለYango ተጠቃሚዎች ዓለም አቀፍ አጠቃላይ የዘመቻ ደንቦች ተገዢ ነው፤ ይህም እዚህ ይገኛል፦ https://yango.com/en_int/lp/usercontest

አዘጋጅ፦ Yango፣ GTOG IT SOLUTIONS SHARE COMPANYን በመወከል። የተመዘገበ አድራሻ፦ 595/596 ወንድሜነህ ጎዳና፣ አራዳ ክፍለከተማ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ።

ግዛት፦ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ወቅት፦ : 15.05.2016 – 06.06.2016

ለተጠቃሚ ዘመቻ ብቁ ለመሆን ሊያሟላቸው የሚገቡ ሁኔታዎች፦ በYango ቢያንስ 1 ጉዞ ከ15.05.2016 – 06.06.2016 ማድረግ።

ሽልማት: አንድ iPhone 15 ስማርትፎን 
6.1 - ኢንች OLED ዲስፕለይ፣ Apple Bionic 16 ፕሮሰሰር፣ 48MP ዋና ካሜራ

የአሸናፊ(ዎች) አመራረጥ፦ ከ15.05.2016 – 06.06.2016 ድረስ ከሁሉም ተጠቃሚዎች ውስጥ ከፍተኛ የጉዞዎች ብዛት ያለው ተጠቃሚ። ከየካቲት 6 በኋላ አሸናፊዎችን እናነጋግራለን።

ሽልማት አሰጣት፡- አዘጋጅ ሽልማቱን በግል ለማስረከብ አሸናፊዎቹን ይጋብዛቸዋል። ሽልማቶችን መቀበያ ቦታ፣ ጊዜ እና ሂደት በተጨማሪነት የምናሳውቅ ይሆናል እንዲሁም በስልክ ጥሪ በኩል እንዲያውቁ ይደረጋል። አዘጋጅ ቢያንስ 2 ጊዜ አሸናፊውን ለማግኘት ይሞክራል። አሸናፊዎቹ ከተገለጹ በኋላ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ከአዘጋጁ ጋር መገናኘት ካልቻሉ፣ አዘጋጅ ከእርስዎ ውጪ አዲስ አሸናፊ የመምረጥ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ገዢ የሆነ ሕግ፦ ይህ የተጠቃሚ ዘመቻ በኢትዮጵያ ሕጎች ተገዢ ነው።

Published 02.10.2023.  © 2023 RideTechnology Global FZ-LLC

This document has been published upon the request and on behalf of G2G IT SOLUTIONS S.C.

ይህ ሰነድ በጂ ቱ ጂ ጥያቄ መሠረት፤ ጂ ቱ ጂ አይቲ ሶሉሽንስን በመወከል ታትሟል።


Fri Sep 06 2024 21:18:06 GMT+0300 (Moscow Standard Time)