የእርስዎ የተሳፋሪ የደረጃ ምደባ የሚወሰነው አሽከርካሪዎችዎ በሰጡት የመጨረሻዎቹ 40 የደረጃ ምደባዎች መሠረት ነው። አዎ፣ ልክ እርስዎ ደረጃ እንደሚሰጧቸው ሁሉ አሽከርካሪዎችዎም ለእርስዎ ደረጃ ይሰጡዎታል።
ውስጥ ያለዎት የደረጃ ምደባ
yango
ሲጀመር የእኔ የደረጃ ምደባ ምን ይሰራል?
እሺ ገባኝ። ግን የእኔ የደረጃ ምደባ ላይ ምን ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል?
በአሽከርካሪዎች እና ተሳፋሪዎች መካከል ጥንቃቄ እና መከባበር ሲኖር ሁሉም አሸናፊ ይሆናል። ስለዚህ Yango ጉዞውን ለመገምገም እና ለሁለቱም ወገኖች አስተያየቶችን ለማካፈል እድል ይሰጣል።
መሰረታዊ የጨዋነት ህጎችን መከተል የደረጃ ምደባዎን ከፍ ሊያደርግ ይችላል። ትንሽ ቢወርድ አይጨነቁ - ፍጹም የሆነ ተሳፋሪ መሆን ያን ያህል ቀላል አይደለም። አፈጻጸምዎን እንዲያሻሽሉ ለማገዝ አንዳንድ ጠቃሚ ምክሮችን ይዘን መጥተናል።
ጠቃሚ ምክሮች ለተሳፋሪዎች
በሰዓትዎ ይገኙ
አሽከርካሪዎች ተሳፋሪን ለረጅም ጊዜ አለመጠበቅን ይመርጣሉ፣ በተለይም ለመኪና ማቆሚያ ምቹ ባልሆኑ ቦታዎች። ጥቆማ፦ ከዘገዩ፣ በውይይት ውስጥ ለአሽከርካሪው ማሳወቅ የተሻለ ነው
ለአሽከርካሪዎ ያስቡላቸው
ለእርስዎ እና ለአሽከርካሪዎ ለሁለታችሁም ምቹ የሆነ የመነሻ ቦታን ይምረጡ። የመነሻ ቦታውን የሚያግዱ ነገሮች ባሉበት፣ በተዘጉ ቦታዎች ወይም አሽከርካሪዎች መኪና ሲያቆሙ ቅጣት በሚቀጡበት ቦታ ላይ ከማድረግ ይቆጠቡ
ይጠንቀቁ
ቀላል ነው፦ በሚዘጉበት ጊዜ በሩን በኃይል አይወርውሩት፣ አያቆሽሹ እንዲሁም ደስ የማይሉ ሽታዎች እና የምግብ ፍርፋሪዎች በመኪናው ውስጥ እንዳይቀሩ ከመብላትና ከማጨስ ይቆጠቡ
የጨዋነት ምግባር ያሳዩ
እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፣ እንዲሁም ውይይቱ ምቾት የሚነሳ ከሆነ በትህትና ለማቋረጥ አያመንቱ። በስልክ የሚደረጉ ጮክ ያሉ ንግግሮችን ለማስወገድ ይሞክሩ (የማይቻሉ ከሆኑ - ለአሽከርካሪው ያሳውቁ)። ሰላም እና ደህና ይሁኑ ማለትን እና አሽከርካሪውን ለጉዞው ማመስገንዎን አይርሱ።
ይሄው ነው በቃ!
በጣም ቀላል፣ አይደል? እነዚህን ቀላል ምክሮች ብቻ ይከተሉ እና በጉዞዎችዎ ይደሰቱ!
Yango ተግባራዊ በሚሆኑ ሕጎች ምክንያት ፈቃድ በተሰጠው ሕጋዊ ግለሰብ የሚቀርብ የመረጃ አገልግሎት ነው፣ እናም እንደ የትራንስፖርት ወይም የታክሲ አገልግሎቶች አቅራቢ ተደርጎ ሊታሰብ አይገባም። የትራንስፖርት አገልግሎቶች የሚቀርቡት በሦስተኛ ወገኖች ነው።
© 2023 GTOG IT SOLUTIONS, S.C.
Fri Sep 06 2024 21:17:50 GMT+0300 (Moscow Standard Time)